News News

Back

በፍጆታ ዕቃዎች ላይ የዋጋ ንረትን ለመቆጣጠር አምራቹና ሸማቹ በጋራ ሊሰሩ ይገባል::

በሸቀጦችና የግብርና ምርቶች ላይ የሚኖረው የዋጋ ጭማሪ የከተማዋንና አካባቢውን ሕብረተሰብ እንዳይጎዳ ከማድረግ ባሻገር የገበያ ግሽበት እንዳይከሰት መቆጣጠር ተገቢ እንደሆነም አመልክተዋል። "የንግድ ትርዒትና ባዛሩ ዓለማ ሕዝባዊ በዓላትን ምክንያት በማድረግ በሸቀጦችና የፍጆታ ዕቃዎች ላይ የዋጋ ጭማሪ እንዳይኖር ከማድረግ ባለፈ አምራችና ሸማቹ በተመጣጣኝ ዋጋ ተጠቃሚ እንዲሆን ማስቻል ነው" ብለዋል ።

ሕብረተሰቡ የግብርና ምርቶችን ጨምሮ ሁሉንም ሸቀጦችና የፍጆታ እቃዎች በአንድ ቦታ በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲያገኝ በማድረግ በኩልም ባዛሩ ፋይዳው የጎላ መሆኑን አመልክተዋል።የአዳማ ከተማ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ፈይሳ አራርሳ በበኩላቸው ባዛሩ በበዓላት ወቅት ሊከሰት የሚችለውን የዋጋ ንረት በማረጋጋት ሕብረተሰቡ እንዳይጎዳ ለማድረግ ሲባል መዘጋጀቱን ገልጸዋል።

የገናና ጥምቀት በዓልን ምክንያት በማድረግ የተዘጋጀው ሀገር አቅፍ የንድግ ትርዒትና ባዛር አምራቹንና ሸማቹን ሕብረተሰብ የሚያቀራርብ መሆኑም ገልጸዋል።በባዛሩ ላይ ከ300 በላይ የንግድ ድርጅቶች ምርቶቻቸውን በማስተዋወቅ ላይ መሆናቸው ታውቋል።

የከተማዋን የንግድ፣ ኢንዱስትሪ፣ ኢንቨስትመንትና የቱሪዝም ፍሰት ለማሳለጥም ሆነ ገቢዋን ለማጠናከር ባዛሩ የጎላ ፋይዳ እንዳለው የገለጹት ደግሞ የአዳማ ከተማ ንግድና ገበያ ልማት ጽህፍት ቤት ኃላፊ አቶ ሻምበል ወርቅነህ ናቸው።ባዛሩ በከተማዋ በበዓላት ወቅት የሚኖረውን ህግ ወጥ የጎዳና ላይ ንግድ ለመከላከልና ለመቆጣጠር ጭምር ፋይዳው የጎላ መሆኑን አስረድተዋል።

በንግድ ትርኢትና ባዛሩ ላይ የግብርና፣ ማኑፋክቸሪንግ፣ የኢንዱስትሪ ውጤቶችና ሌሎች ተዛማጅ ምርቶች በተመጣጣኝ ዋጋ በመሸጥ ላይ በመሆናቸው ሕብረተሰቡ ተጠቃሚ እንዲሆን አቶ ሻምበል አመልክተዋል።በንግድ ትርዒትና ባዛሩ ላይ ሲሸምቱ የተገኙት አቶ ዳምጠው አለሙ ሁሉም የፍጆታ እቃዎችና ሸቀጦች በተመጣጣኝ ዋጋ በባዛሩ ላይ መቅረባቸውን ተናግረዋል።

በባዛሩ ላይ ምርቶች ይዘው ከቀረቡት መካከል አቶ ተስፋዬ ባለሚ በበኩላቸው በከተማዋ በሚካሄደው የንግድ ትርዒትና ባዛር ላይ መሳተፍ ከጀመሩ ስምንት ዓመት እንደሆናቸው ገልጸዋል። ተጨማሪ ለማንበብ http://www.ena.gov.et

Average (0 Votes)


No comments yet. Be the first.

News Archive News Archive