News News

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ ከንግዱ ማኅበረሰብ ጋር እየተወያዩ ነው :: ሚያዝያ 8/2010

አዲስ አበባ ሚያዝያ 8/2010 ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከንግዱ ማኅበረሰብ ለመተዋወቅና በዘርፉ በሚያጋጥሙ ችግሮች ላይ ለመምከርና የጋራ የመፍትሔ አቅጣጫ ለማስቀመጥ የሚያስችል መድረክ በአዲስ አበባ ተጀምሯል።

የመድረኩ የውይይት መነሻ እንዲሆን በንግድ ማኅበረሰብ ተወካዮች በንግድ ዘርፍ ያጋጠሙ ችግሮች ለጠቅላይ ሚኒስትሩ እየቀረቡ ነው።የውጭ ምንዛሬ አቅርቦትና አጠቃቅም፣ የገንዘብ አቅርቦት፣ የመንግስት ተቋማት አገልግሎት አሰጣጥ፣ ያልተገባ የንግድ ውድድር፣ ከነበረው አገራዊ አለመረጋጋት ጋር ተያይዞ የነበረ የኢንቨስትመንት ዋስትና ችግሮች፣ እንዲሁም የፕራይቬታይዜሽን አለመጎልበት፣ መንግስት ለእርሻ ሜካናይዜሽንም የሚጠበቀውን ድጋፍ አለማድረግ ከተነሱ ችግሮች መካከል ይጠቀሳሉ።

የዘርፉ ተወካዮች ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከንግዱ ማኅበረሰብ ጋር ቅድሚያ ሰጥተው መወያያታቸው ወደፊት ዘርፉ ለሚያጋጥመው ችግር መንግስት እንዲያስተካክልና እነሱም የሚጠበቅባቸውን ሚና እንዲወጡ ያግዛል ብለዋል።ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመድረኩ ለሚነሱ የዘርፉ ጉዳዮች ምላሽ ከመስጠት ባሻገር በዘርፉ መንግስት ወደፊት የሚከተላቸውን አቅጣጫዎችን ይገልጻሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ከተሾሙበት ዕለት ጀምሮ የአገሪቱን ዘርፈ ብዙ ችግር ለመፍታት ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል ያሳተፈ እንቅስቃሴ ለማድረግ የሚያስችል የውይይትና የትውውቅ መድረክ እየተፈጠረ እንደሆነ ይታወቃል።

በትናንትናው ዕለት 25ሺህ ከሚደርሱ የወጣቶችና የተለያዩ ህብረተሰብ ክፍል ተወካዮች ጋር በሚሌኒየም አዳራሽ ትውውቅና ውይይት ማድረጋቸው ይታወሳል። 

ምንጭ ፡ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት

Average (0 Votes)


No comments yet. Be the first.

News Archive News Archive