News News

Back

የአገሪቱን የቴሌቪዥን ስርጭት ጥራትና ተደራሽነት ማሻሻል የሚያስችል ስምምነት ተፈረመ::

የኢንፎርሜሽን ደህንነት መረብ ኤጄንሲ የአገሪቱን የቴሌቪዥን ስርጭት ጥራትና ተደራሽነት ለማሻሻል የሚያስችል የዲጂታላይዜሽን ትግበራ ስምምነት ተፈራረመ።

ስምምነቱ ከአናሎግ ወደ ዘመናዊ የዲጂታል ቴክኖሎጂ ሽግግር ከፍ የሚያደርግ ሲሆን ደህንነቱንም ለመጠበቅ የሚያስችል ነው ተብሏል።

ስምምነቱ ጌትስ ኤር በተባለው የአሜሪካ ኩባንያና የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲን በወከለው በመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት መካከል ተከናውኗል።

በስምምነቱ መሰረት ከአናሎግ ወደ ዲጂታል የመቀየሩ ስራ ከ34 ሚሊዮን ዶላር በላይ ወጪ ይደረግበታል ተብሏል።

ፕሮጀክቱ የቴክኖሎጂ ሽግግርን ማዕከል ያደረገና አገራዊ አቅምን ለማዳበር በሚያስችል መልኩ እንደተከናወነ አስተባባሪው አቶ ጎሳ ደምሴ ተናግረዋል።

የተለያዩ ባለድርሻ አካላትን በማሳተፍ የሚከናወነው የዲጂታላይዜሽን ስርጭት ሂደትም በሦስት ዋና ዋና ምዕራፎች የሚጠናቀቅ እንደሆነ ነው አቶ ጎሳ የገለጹት።

ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ ከ22 በላይ አዳዲስ ጣቢያዎች እንደሚፈጠሩና ማሻሻያ የተደረገባቸው አዳዲስ ከሚገነቡት ጋር በጥምረት ደረጃውን የጠበቀ አገልግሎት እንደሚሰጡ አስታውቀዋል።

በኢትዮጵያ የዲጂታል ቴሌቪዥን ስርጭት ተግባራዊ መደረግ ብዝኃነትን ያማከለ ስርጭትና ተደራሽነት ለመፍጠር እንደሚያስችልም አስተባባሪው ተናግረዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ http://www.ena.gov.et


News Archive News Archive