Government Service Requriements Government Service RequriementsGovernment Services Government Services

Back

የስም ዝውውር በውርስ

አገልግሉት ለማግኘት የሚያስፈልጉ መስፈርች

 • የወራሽነት ማረጋገጫ ማስረጃ በፍ/ቤት የፀደቀ ዋናውን
 • የወራሽነት ወቅታዊ መኖሪያ መታወቂያ ዋናውና ፎቶ ኮፒ
 • በአውራሽ ስም ቀደም ሲል የተሠጠ የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ወይም የቤት ባለቤትነት ማረጋገጫ ደብተር ዋናውና ፎቶ ኮፒ አሟልተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል

አገልግሎቱን ለማግኘት የሚከናወኑ ሂደቶች

 1. ፎርም መውሰጃ ቢሮ በመሄድ የስም ዝውውር ፈቃድ ፎርም ወስዶ መሙላት
 2. የተሞላውን ፎርም በዛው ቢሮ የሚገኝ ባለሙያ ይሠጣል
 3. የተሞላውን ፎርም በዛው ቢሮ የሚገኝ ባለሙያ ይመረምራል
 4. ፎርሙን ከተመለከተ በኋላ ፋይል መጠየቂያ ካርድ ይሠጣቸዋል
 5. የፋይል ማውጫውን ካርድ በመያዝ መዝገብ ቤት መስጠት
 6. መዝገብ ቤት መዝገቡን የይዞታ አስተዳደር ቢሮ በመውሰድ ለባለሙያው ይሠጣል
 7. ባለሙያው መዝገቡን በመመልከት የክፍያ ዝርዝር ያወጣል
 8. የወጣውን የክፍያ ዝርዝር ለባለጉዳዩ ይሠጠዋል
 9. በዛው ቢሮ የአገልግሎት ክፍያ ይከናወናል
 10. የከፈለውን ደረሰኝ በዛው ቢሮ ይገባል
 11. የፕላንና ይዞታ ማረጋገጫ ቢሮ ባለሙያ ለባለ ጉዳዩ የስም ዝውውሩንና ፕላኑን ያስረክባል