ወደ ሕገ መንግስት ዋና ገጽ
ምዕራፍ አሥር : የብሔራዊ ፖሊሲ መርሆዎችና ዓላማዎች
አንቀጽ 85 ዓላማዎች
-
ማንኛውም የመንግሥት አካል ሕገ መንግሥቱን፣ ሌሎች ሕጐችንና ፖሊሲዎችን ሥራ ላይ ሲያውል በዚህ ምዕራፍ በተመለከቱት መርሆዎችና ዓላማዎች ላይ መመስረት አለበት፡፡
-
በዚህ ምዕራፍ ውስጥ «መንግሥት» ማለት እንደየሁኔታው የፌዴራል መንግሥት ወይም የክልል መስተዳድሮች ማለት ይሆናል፡፡
አንቀጽ 86 የውጭ ግንኙነት መርሆዎች
-
የኢትዮጵያ ሕዝቦች ጥቅም የሚያስጠብቅና የሀገሪቱን ሉዓላዊነት የሚያስከብር የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ ማራመድ፡፡
-
የመንግሥታትን ሉዓላዊነትና እኩልነት ማክበር፣ በሌሎች ሀገሮች ጉዳዮች ውስጥ ጣልቃ አለመግባት፡፡
-
የሀገሪቱ የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ በጋራ ጥቅምና በእኩልነት ላይ የተመሰረተ መሆኑን እንዲሁም በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚደረጉ ስምምነቶች የኢትዮጵያን ጥቅም የሚያስከብሩ መሆናቸውን ማረጋገጥ፡፡
-
የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት የሚያስከብሩና የሕዝቦኟን ጥቅም የማይጻረሩ ዓለም አቀፍ ሕጐችና ስምምነቶችን ማክበር፡፡
-
ከጐረቤት ሀገሮችና ከሌሎችም የአፍሪካ ሀገሮች ጋር በየጊዜው እያደገ የሚሄድ ኢኮኖሚያዊ ኅብረትና የሕዝቦች ወንድማማችነትን ማጐልበት፡፡
-
በሀገሮች መካከል የሚነሱ ግጭቶች ሰላማዊ በሆነ መንገድ እንዲፈቱ ጥረት ማድረግ፡፡
አንቀጽ 87 የመከላከያ መርሆዎች
-
የሀገሪቱ የመከላከያ ሠራዊት የብሔሮች፣ የብሔረሰቦች እና የሕዝቦችን ሚዛናዊ ተዋጽኦ ያካተተ ይሆናል፡፡
-
የመከላከያ ሚኒስትር ሆኖ የሚሾመው ሲቪል ይሆናል፡፡
-
የመከላከያ ሠራዊት የሀገሪቱን ሉዓላዊነት ከመጠበቅ በተጨማሪ በዚህ ሕገ መንግሥት መሰረት በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የሚሰጡትን ተግባሮች ያከናውናል፡፡
-
የመከላከያ ሠራዊቱ በማናቸውም ጊዜ ለሕገ መንግሥቱ ተገዢ ይሆናል፡፡
-
የመከላከያ ሠራዊቱ ተግባሩን ከፖለቲካ ድርጅቶች ወገናዊነት ነጻ በሆነ አኳኊን ያከናውናል፡፡
አንቀጽ 88 ፖለቲካ ነክ ዓላማዎች
-
መንግሥት በዴሞክራሲያዊ መርሆዎች ላይ በመመሥረት ሕዝቡ በሁሉም ደረጃዎች ራሱን በራሱ የሚያስተዳድርበትን ሁኔታ ማመቻቸት አለበት፡
-
መንግሥት የብሔሮችን፣ የብሔረሰቦችን፣ የሕዝቦችን ማንነት የማክበርና በዚሁ ላይ በመመርኮዝ በመካከላቸው እኩልነት፣ አንድነትና ወንድማማችነትን የማጠናከር ግዴታ አለበት፡፡
አንቀጽ 89 ኢኮኖሚ ነክ ዓላማዎች
-
መንግሥት ሁሉም ኢትዮጵያውያን የሀገሪቱ የተጠራቀመ እውቀትና ሀብት ተጠ ቃሚዎች የሚሆኑበትን መንገድ የመቀየስ ኃላፊነት አለበት፡፡
-
መንግሥት የኢትዮጵያውያንን የኢኮኖሚ ሁኔታዎች ለማሻሻል እኩል ዕድል እንዲኖራቸው ለማድረግና ሀብት ፍትሐዊ በሆነ መንገድ የሚከፋፈሉበትን ሁኔታ የማመቻቸት ግዴታ አለበት፡፡
-
የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋ እንዳይደርስ መከላከልና አደጋው ሲደርስም ለተጐጂው እርዳታ በወቅቱ እንዲደርስ ማድረግ፡፡
-
በእድገት ወደኊላ ለቀሩ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች፣ ሕዝቦች መንግሥት ልዩ ድጋፍ ያደርጋል፡፡
-
መንግሥት መሬትንና የተፈጥሮ ሀብትን በሕዝብ ሥም በይዞታው ሥር በማድረግ ለሕዝቡ የጋራ ጥቅምና እድገት እንዲውሉ የማድረግ ኃላፊነት አለበት፡፡
-
የሀገር ልማት ፖሊሲዎችና ኘሮግራሞች በሚዘጋጁበት ወቅት መንግሥት ሕዝቡን በየደረጃው ማሳተፍ አለበት፡፡ የሕዝብንም የልማት እንቅስቃሴዎች መደገፍ አለበት፡፡
-
መንግሥት በሀገር ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ልማት እንቅስቃሴ ውስጥ ሴቶች ከወንዶች ጋር በእኩልነት የሚሳተፉበትን ሁኔታ የማመቻቸት ኃላፊነት አለበት፡፡
-
መንግሥት የሠራተኛውን ሕዝብ ጤንነት፣ ደህንነትና የኑሮ ደረጃ ለመጠበቅ መጣር አለበት፡፡
አንቀጽ 90 ማኅበራዊ ነክ ዓላማዎች
-
የሀየሀገሪቱ አቅም በፈቀደ መጠን ሁሉም ኢትዮጵያዊ የትምህርት፣ የጤና አገልግሎት፣ የንoህ ውሃ፣ የመኖሪያ፣ የምግብና የማኅበራዊ ዋስትና እንዲኖረው ይደረጋል፡፡
-
ትምህርት በማናቸውም ረገድ ከሃይማኖት፣ ከፖለቲካ አመለካከቶች እና ከባህላዊ ተፅእኖዎች ነጻ በሆነ መንገድ መካሔድ አለበት፡፡
አንቀጽ 91 ባሕል ነክ ዓላማዎች
-
መንግሥት መሰረታዊ መብቶችንና ሰብዓዊ ክብርን፣ ዴሞክራሲንና ሕገ መንግሥቱን የማይቃረኑ ባሕሎችና ልማዶች በእኩልነት እንዲጐለብቱና እንዲያድጉ የመርዳት ኃላፊነት አለበት፡፡
-
የሀገር የተፈጥሮ ሀብቶችንና የታሪክ ቅርሶችን መጠበቅ የመንግሥትና የሁሉም ኢትዮጵያዊ ግዴታ ነው፡፡
-
መንግሥት አቅም በፈቀደ መጠን ኪነጥበብን፣ ሳይንስንና ቴኖሎጂን የማስፋፋት ግዴታ አለበት፡፡
አንቀጽ 92 የአካባቢ ደህንነት ጥበቃ ዓላማዎች
-
መንግሥት ሁሉም ኢትዮጵያዊ ንoሕና ጤናማ አካባቢ እንዲኖረው የመጣር ኃላፊነት አለበት፡፡
-
ማንኛውም የኢኮኖሚ ልማት እርምጃ የአካባቢውን ደህንነት የሚያናጋ መሆን አለበት፡፡
-
የሕዝብን የአካባቢ ደህንነት የሚመለከት ፖሊሲና ኘሮግራም በሚነደፍበትና ሥራ ላይ በሚውልበት ጊዜ የሚመለከተው ሕዝብ ሁሉ ሐሳቡን እንዲገልጽ መደረግ አለበት፡፡
-
መንግሥትና ዜጐች አካባቢያቸውን የመንከባከብ ግዴታ አለባቸው፡፡