Embelem of Federal Democratic Republic of Ethiopia Official Portal of Federal  Democratic Republic of Ethiopia  
Home Home Citizens Citizens Government Government Businesses Businesses Forigners Forigners NGOs NGOs Decrease font Increase font
 

 ሰሌታዊ ገጽታ

·   ኦፊሴላዊ ስም፡ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት

·   ርእሰ ከተማ፡ አዲስ አበባ

·   የመልክአ ምድር አቀማመጥ፡ ኢትዮጵያ በምስራቅ አፍሪካ በልዩ አጠራሩ “የአፍሪካ ቀንድ” በሚባለው የአፍሪካ ክፍል ትገኛለች፡፡ በምስራቅ ከጅቡቲ እና ሶማሊያ፣ በሰሜን ከኤርትራ፣ በምዕራብ ከሱዳን እንዲሁም  በደቡብ ከኬንያ ጋር ትዋሰናለች፡፡

·   መገኛ ቦታ፡ ኢትዮጵያ ከምድር ወገብ ከ 3o እስከ 15o በሰሜን፣ እና 33o – 48o  በምስራቅ ከግሪንዊች ሜሪድያን ትገኛለች፡፡

·   የቆዳ ስፋት:            

·         አጠቃላይ የቆዳ ስፋት፡ 1.14 ሚሊዮን ስኩዌር ኪ.ሜትር

·         ሊታረስ የሚችለው መሬት፡ 45%

·         በመስኖ ሊለማ የሚችል: 10 ሚሊዮን ሄክታር

·         በመስኖ የለማ: ወደ  3%

·   ስነ-ህዝብ  

· ጠቅላላ የህዝብ ቁጥር: ወደ 80 ሚሊዮን

o    የሴቶች ቁጥር፡ 39.9 ሚሊዮን

o    የወንዶች ቁጥር:40.1 ሚሊዮን

  በገጠር የሚኖር: 66.8 ሚሊዮን

  በከተማ የሚኖር:13.2 ሚሊዮን

  የህዝብ ቁጥር ዕድገት በአመት: 2.73%

  የህዝብ ጥግግት:66.5:1 ስኩ.ኪ.ሜ       

·   አማካኝ የአንድ ሰው የእድሜ ጣሪያ

o    ወንድ: 53.42 ዓመት

o    ሴት:55.42 ዓመት

·  የዕድሜ ስብጥር (በመቶኛ)

o    0-14: 42.8%

o    15-19: 10.5%

o    20-49: 37.4%

o    50-59: 4.9%

o    60 and above: 4.4%

· የስራ ዕድሜ ክልል (በመቶኛ)

o    በከተማ: 54.7%

o    በገጠር: 50.6%

·  ቋንቋ: አራት ዋና ዋና የቋንቋ ቤተሰቦች ሲገኙ በአንድነት ወደ 80 ቋንቋዎች በሀገሪቱ ይነገራሉ

§    የስራ ቋንቋ፡ አማርኛ

§      የእንግሊዝኛ ቋንቋም ለቢዝነስ እንቅስቃሴዊች ለባንክ፣ ለኢንሹራንስ መስሪያ ሲሆን የከፍተኛ ትምህርት ማስተማሪያም በመሆን ያገለግላል፡፡

·  ዋነኛ ሀይማኖቶች፡ ክርስትና እና እስልምና

·  የመንግስት አወቃቀር፡ ፌዴራላዊ ሲሆን በ9 ክልላዊ መንግሰታት እና በሁለት የከተማ መስተዳደር የተዋቀረ ነው፡፡

·  ብሄራዊ የህግ አውጭ አካል፡ ፓርላማ፣ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት ናቸው፡፡

·   ምርጫ፡ በየአምስት አመቱ

·  ከፍታ፡ ኢትዮጵያ ከ148 ሜትር ከባህር ጠለል በታች ከሚገኘው የዳሎል ዝቅተኛ ቦታ እስከ 4620 ሜትር የባህር ጠለል በላይ ከፍታ እሰካለው የራስ ዳሸን ተራራ የሚደርስ የከፍታ ልዩነት አላት፡፡

·  የአየር ንብረት፡ የሙቀት መጠኑ ከ20 oC እስከ 30 oC ይደርሳል፡፡ የዝናብ መጠኑ ከ200ሚ.ሜ እስከ 2000ሚሜ በአመት ይደርሳል፡፡

·  የሰዓት አቆጣጠር፡ ጂኤምቲ +3

·  ዝናባማ ወቅቶች፡ ኢትዮጵያ ከፍተኛ የዝናብ መጠን የሚኖራት በሰኔ፣ ሀምሌና ነሀሴ ሲሆን በየካቲትና መጋቢት አነስተኛ የዝናብ መጠን ይኖራታል፡፡

·  የመገበያያ ገንዘብ:

· ትንሹ የገንዘብ መለኪያስ: ብር

·  1 ብር= 100 ሳንቲሞች

·  የብር ኖቶች፡ ባለ 1 5 10 50 እና 100 ብር

·  የመዳብ ሳንቲሞች፡ 151025፣ እና 50 ሳንቲሞች

·  የውጭ ምንዛሬ አገልግሎት በአየር መንገዶች እና ፈቃድ ባለቸው ሆቴሎች ይገኛል፡፡

 

©የቅጂ መብት 2003 የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት
የግላዊ ጉዳይ ጥበቃ ፖሊሲ |  የአጠቃቀም ደንቦች |  ኃላፊነትን ስለመወሰን | 
ተደራሽነት |  የደንበኞች ቻርተር