Embelem of Federal Democratic Republic of Ethiopia Official Portal of Federal  Democratic Republic of Ethiopia  
Home Home Citizens Citizens Government Government Businesses Businesses Forigners Forigners NGOs NGOs Decrease font Increase font
 

 መልክአ ምድር

ኢትዮጵያ በሰሜን ምስራቅ አፍሪካ 3-14 ዲግሪ ሰሜን እና 33-48 ዲግሪ ምሥራቅ የምትገኝ አገር ስትሆን የቆዳ ስፋቱዋም 1,127,127 ካሬ .. ነው። በሰሜን ከኤርትራ፣ በምዕራብ ከሱዳን፣ በደቡብ ከኬኒያ፣ እንዲሁም በምሥራቅ ከጅቡቲ እና ከሶማሊያ ጋር ትዋሰናለች። የኢትዮጵያ አብዛኛው ግዛት በተራሮችና በሀይቆች የተሞላ ሲሆን፣ ታላቁ የምሥራቅ አፍሪካ ስምጥ ሸለቆ እነዚህኑ ከፍተኛ ቦታዎች ከሰሜን ምሥራቅ ወደ ደቡብ ምዕራብ በመጋደም ለሁለት ይከፍላቸዋል። በስምጥ ሸለቆው ዙሪያም በረሃማ የሆኑ ዝቅተኛ ቦታዎች ይገኛሉ። ይኅን መሰሉ የመልክዓ-ምድር ልዩነት አገሪቷ የተለያዩ የአየር ንብረት፣ የአፈር፣ የዕፅዋት እና የሕዝብ አሰፋፈር ገጽታዎች እንዲኖራት አስችሏታል። በከፍታና በመልክዓ ምድራዊ አቀማመጥ የተነሣ በኢትዮጵያ ውስጥ ሦስት ዐይነት የአየር-ንብረት ክልሎች ይገኛሉ። እነሱም:-

  • ደጋ - ከፍታቸው ከባሕር ጠለል 2400 ሜትር የሚጀምር እና የሙቀት መጠናቸው 16 ዲግረ . የማይበልጥ፤
  • ወይናደጋ - ከፍታቸው ከባሕር ጠለል 1500 እስከ 2400 ሜትር፣ ሙቀታቸውም 16 ዲግረ . እስከ 30 ዲግረ . የሚደርስና፣
  • ቆላ - ከባህር ጠለል በታች ጀምሮ እስከ 1500 ሜትር ከፍታ ያላቸው፣ የሙቀት መጠናቸውም 30 ዲግረ . እስከ 50 ዲግረ . የሚደርስ አከባቢዎች ናቸው።

ዋናው የዝናብ ወቅት ከሰኔ አጋማሽ እስከ መስከረም አጋማሽ ሲሆን፣ ከሱ ቀደም ብሎ አልፎ አልፎ የሚጥል የበልግ ዝናብ በየካቲት እና በመጋቢት ይከሰታል። የተቀሩት ወራት በአብዛኛው ደረቅ ናቸው።

 

©የቅጂ መብት 2003 የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት
የግላዊ ጉዳይ ጥበቃ ፖሊሲ |  የአጠቃቀም ደንቦች |  ኃላፊነትን ስለመወሰን | 
ተደራሽነት |  የደንበኞች ቻርተር