Embelem of Federal Democratic Republic of Ethiopia Official Portal of Federal  Democratic Republic of Ethiopia  
Home Home Citizens Citizens Government Government Businesses Businesses Forigners Forigners NGOs NGOs Decrease font Increase font
 

 መሰረተ ልማት

 

መንገዶች

የዩናይትድ ኪነግደምን አምስት እጥፍ በምትሆን ሀገር፣ ነገር ግን ሀገሪቷን ሊያዳርስ የሚችል የባቡር መስመር በሌለበት ሁኔታ የመንገድ ትራንስፖርት የሚጫወተው ሚና ቀላል አይደለም፡፡ ላለፉት ሰባት አመታት ለመንገድ ግንባታው ዘርፍ ልዩ ትኩረት እና ከፍተኛ በጀት ተመድቦለታል፡፡ ሀገሪቱ ለመንገድ ስራ የምትመድበው በጀት ከጠቅላላው የሀገሪቱ በጀት ሲሶውን ይይዛል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የኢትዮጵያ መንግስት በመንገድ ልማት ዘርፍ ፕሮግራሙ ለመንገዶች ስራ፣ ጥገና  ማሳደግ ወደ 4 ቢሊዮን ዶላር ድጎማ ያደርጋል፡፡ ይህ የሚያሳየው መንግስት ለመንገድ ስራ ከፍተኛ ትኩረት መስጠቱን እና የሀገሪቱን እምቅ ሀብት በከፍተኛ ደረጃ ለመጠቀም የሚያደርገውን ጥረት ነው፡፡

መንግስት በቀጣዮቹ አምስት አመታት 3‚833 ኪ.ሜ የአስፓልት፣ 1‚390 ኪሜ መጋቢ መንገድ እና 5‚399 ኪ.ሜ የጠጠር መንገዶችን ሰርቷል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ 2‚613 ኪ.ሜ የአስፓልት፣ 1‚575 ኪ.ሜከፍተኛ የጠጠር መንገዶች እድሳት አከናውኗል፡፡ 

ከፍተኛ ትኩረት የተሰጣቸው ከመዲናዋ አዲስ አበባ ወደ ጅማ፣ አዋሳ፣ አዲግራት፣ እና ጅቡቲ መንገዶች ስራ ይገኙበታል፡፡ ይህንን የመንገድ ስራ ለማስጀመርም 309 ሚሊዮን ዶላር ከአለም ባንክ፣ 300 ሚሊዮን ዶላር ከአውሮፓ ህብረት፣ 104 ሚሊዮን ዶላር ከአፍሪካ ልማት ባንክ የተገኘ ሲሆን፤ የኢትዮጵያ መንግስትም 940 ሚሊዮን ዶላር ፈሰስ አድረጓል፡፡ ከዚህም ጋር ተያይዞ ከአዲስ አበባ - ጅማ 326 ኪ.ሜ እና ከአዲስ አበባ - ወልድያ 513 ኪ.ሜ መንገዶች ለመጀመር በዝግጅት ላይ ይገኛል፡፡ 

የአየር ትራንስፖርት አገልግሎት

የኢትዮጵያ አዳዲስ እና የተሻሻሉ አየር መረፊያ ጣቢያዎች መንገደኞችንና እቃዎችን ወደ ሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጭ ለማጓጓዝ ምቹ ናቸው፡፡ ይህም ሀገሪቱ ለይ የሚደረግን ኢንቨስትመንት የሚያበረታታ ነው፡፡ በአሁኑ ወቅትም ሀገሪቱ ሁለት አለም አቀፍ አየር ማረፊያዎች ያሏት ሲሆን (የአዲስ አበባ እና የድሬዳዋ) እነዚሁም አየር ማረፊያዎች ላለፉት ጥቂት አመታት አያሌ ተጓዦችንና ዕቃዎችን አስተናግደዋል፡፡ አዲስ የካርጎ ማሰተላለፊያ ተርሚናሎች በአዲስ አበባና ድሬዳዋ ከተሞች የተገነቡ ሲሆን በስራ ላይ ውለውም አገልግሎት መስጠት ጀምረዋል፡፡ የቱሪዝም እንቅስቃሴን ለማበረታታትም የአርባ ምንጭ፣ ላሊበላ፣ መቀሌ፣ አክሱም እና ጎንደር አየር ማረፊያዎች ተሻሽለው ተሰርተዋል፡፡ አዲስ አየር ማረፊያ በአርባ ምንጭ መገንባቱም በለምለሙ የደቡብ ክፍል አዲስ የኢኮኖሚ መነቃቃት እና ማንሰራራት እድል የከፈተ ነው፡፡ 

ቴሌኮሙኒኬሽን

ኢትዮጵያ የነበሯትን 160‚000 ውስን የስልክ መስመሮች በከፍተኛ ቁጥር ለማሳደግና አገልግሎቱንም አብዛኛው የህዝብ ቁጥር ወዳለበት የገጠሩ አካባቢዎች ለማዳረስ ከትልቅ ኃላፊነት ጋር ተጋፍጣለች፡፡ በ1996 የኢትዮጵያ ቴሌኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ለሁለት ተከፍሎ በአዲስ ተዋቅሯል፡፡ የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የኢንዱስትሪውን አካሄድ ሲቆጣጠር፣ የቴሌኮሙኒኬሽን ኮርፖሬሽን ደግሞ የቴሌኮም አገልግሎትን ማዳረስ ጥራቱን መከታተል እና የማስፋፋት ስራዎችን ይሰራል፡፡

ስልጣንን ለክልል መንግስታት ለማውረድ በተደረገው ፖሊሲ መሰረት የኢትዮጵያ ቴሌኮሙኒኬሽን ኮርፖሬሽን በክልል ደረጃ ተዋቅሯል፡፡ በዚህም መሰረት እያንዳንዱ የክልል መንግስት የቴሌኮም አገልግሎትን ለዜጎች የማዳረስ ኃላፊነት ተሰጥቶታል፡፡


 

©የቅጂ መብት 2003 የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት
የግላዊ ጉዳይ ጥበቃ ፖሊሲ |  የአጠቃቀም ደንቦች |  ኃላፊነትን ስለመወሰን | 
ተደራሽነት |  የደንበኞች ቻርተር