Embelem of Federal Democratic Republic of Ethiopia Official Portal of Federal  Democratic Republic of Ethiopia  
Home Home Citizens Citizens Government Government Businesses Businesses Forigners Forigners NGOs NGOs Decrease font Increase font
 

 ህዝብ

ኢትዮጵያ 80 በላይ የሚሆኑ ብሄር ብሄረሰቦች የሚገኙባት «የብሄረሰቦች ሙዚየም» ልትሰኝ የምትችል ሀገር ነች።  የኦሮሞ፣ የአማራ፣ እና የትግራይ እንዲሁም የሶማሌ ብሄረሰቦች ከጠቅላላው የአገሪቱዋ ሕዝብ ቁጥር 3/4 በላይ የሚሆነውን ይይዛሉ። በሃይማኖት በኩልም ክርስትናና  እስልምና በስፋት የሚስተዋልባት አገር ናት። እስልምና 25-30% የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ተከታዮች 60-65% ፡ ፐሮቴስታንት ደግሞ 10% የሚሆነውን ድርሻ ይሸፍናል።

ቋንቋዎች

በኢትዮጵያ ውስጥ 80 በላይ ብሄር ብሄረሰቦች የሚኖሩ ሲሆን በቋንቋም በኩል 80 በላይ የሚሆኑ ቋንቋዎች የሚነገርባት ሀገር ናት፡፡ በአሁኑ ወቅት በእብዛኛው ኢትዮጵያውያን የሚነገሩት ቋንቋዎች አማርኛ እና ኦሮምኛ ሲሆኑ፤ አማርኛ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍል ያሉ ነዋሪዎች የመማሪያ፤ የመገበያያ እንዲሁም የስራ ቋንቋ ሆኖ የቆየ በመሆኑ በአሁኑ ወቅት የብሄራዊ ቋንቋ ነው። በኢትዮጵያ የሚነገሩት ቋንቋዎች ወደ አራት ዋና ዋና የቋንቋ ክፍሎች ሊካተቱ ይችላሉ። እነዚሁም:-

  • ኩሻዊ: ወደ 19 ቋንቋዎችን የያዘ
  • የአባይ-ሰሃራዊ: ወደ 20 ቋንቋዎችን የያዘ
  • ኦሞአዊ: ወደ 23 ቋንቋዎችን የያዘ
  • ሴማዊ: ወደ 12 ቋንቋዎችን የያዙ ናቸው።

ኩሻዊ ከሚባሉት ቋንቋዎች ዋና ዋናዎቹ ኦሮምኛ፣ ሶማልኛ፣ አፋርኛ፣ ሲዳምኛ፣ ሃዲያኛ እና ከምባትኛ ሲሆኑ አባይ-ሰሃራዊ የቋንቋ ምድብ የሚካተቱት በርታኛ፣ ኩናማኛ፣ ጉሙዝኛ፣ ሙርሲኛ እና የመሳሰሉት ናቸው። እንደ ወላይትኛ ጋሞኛ፣ ከፋኛ፣ ሃመርኛ የመሳሰሉት ኦሞአዊ ቋንቋ ዘሮች ሲሆኑ አማርኛ፣ ትግርኛ፣ ጉራጊኛ፣ ስልጢኛ፣ ሀደሪኛ እና መሰል ቋንቋዎች ሴማዊ ቋንቋዎች ይመደባሉ።

የሴሚቲክ ምንጭ ያላቸው እንደ አማርኛ ያሉት ቋንቋዎች የራሱ የሆነ የተለየ የፊደል ስርአት ያላቸው ሲሆን ይህም ኢትዮጵያን ከአፍሪካ ብቸኛዋ ባለ ጥንት ፊደል ሀገር ያደርጋታል። እነኚህ የሴሚቲክ ምንጭ ያላችው ቋንቋዎች ግዕዝ የተባለ በአሁኑ ወቅት ከቤተክርስትያን ውጭ ለእለት ተእለት ግልጋሎት ላይ የማይውል ግንድ ዘር አላቸው።

 

©የቅጂ መብት 2003 የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት
የግላዊ ጉዳይ ጥበቃ ፖሊሲ |  የአጠቃቀም ደንቦች |  ኃላፊነትን ስለመወሰን | 
ተደራሽነት |  የደንበኞች ቻርተር