Embelem of Federal Democratic Republic of Ethiopia Official Portal of Federal  Democratic Republic of Ethiopia  
Home Home Citizens Citizens Government Government Businesses Businesses Forigners Forigners NGOs NGOs Decrease font Increase font
 

 የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት

የክልል መንግስታት ዋና ገጽ


Afar Regional Stateየአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በ5 አሰተዳደራዊ ዞኖች፣ በ129 ወረዳዎችን በ28 ከተማዎች የተዋቀረ ነው፡፡ የገጠሩ የክልሉ ክፍል 326 የገበሬ ማህበራት ሲኖሩት የከተማው ክፍል 32 ቀበሌዎች አሉት፡፡ የአፋር ክልል በአርኮሎጂካል ጥናት መሰረት የሰው ልጅ መገኛ ቦታ ሲሆን፣ በቅርቡም 4.4 ሚሊዮን ዓመት እድሜ ያለው ቅሪት አካል ተገኝቷል፡፡

ርእሰ ከተማ

ሰመራ የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርእሰ ከተማ ነች፡፡

የስፍራው አቀማመጥ

የአፋር ክልል በምስራቁ የኢትዮጵያ ክፍል ይገኛል፡፡ በሰሜን ምስራቅ ከኤርትራ፣ በሰሜን - ምዕራብ ከትግራይ ክልል፣ በደቡብ ምዕራብ ከአማራ ክልል፣ በደቡብ ከኦሮሚያ ክልል፣ በደቡብ - ምስራቅ ከሶማሌ ክልል  እንዲሁም በምስራቅ ከጂቡቲ ጋር ይዋሰናል፡፡

የቆዳ ስፋት

የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት 270,000 ስኩ.ኪ.ሜ የሚገመት የቆዳ ስፋት ይሸፍናል፡፡

ስነ-ህዝብ

በ1994 በተገኘው የህዝብ ቆጠራ መሰረት የአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የህዝብ ብዛት 1,106,383 ሲሆን ከዚህም ውስጥ 626,839 ወንዶች እና 479,544 ሴቶች ናቸው፡፡ 1,020,504 (89.5 ከመቶ) የሚሆነው በገጠራማው የክልሉ ቦታዎች ይኖራል፡፡ በሀይማኖት ረገድም 96 ከመቶ የእስልምና፣ 3.86 ከመቶ የኦርቶዶክስ ክርስትያን፣ 0.43 ከመቶ የፕሮቴስታንት፣ 0.09 ከመቶ የካቶሊክ እንዲሁም ሌሎች ሀይማኖት ተከታዮች 0፣02 ከመቶ የሌሎች እምነት ተከታዮች ናቸው፡

በብሄር ስብጥር አኳያም 91.8 ከመቶ የአፋር፣ 4.5 ከመቶ የአማራ፣ 0.92 ከመቶ የአርጎባ፣ 0.82 ከመቶ የትግራዊ፣ 0.8 ከመቶ የኦሮሞ፣ እንዲሁም 0.013 ከመቶ የሀዲያ ብሄረሰቦች ይኖራሉ፡፡

የአፋርኛ ቋንቋ የክልሉ የስራ ቋንቋ ሲሆን 91.8 ከመቶ በክልሉ ይነገራል፣ አማርኛ 6.68 ከመቶ፣ ትግርኛ 0.74 ከመቶ፣ ኦሮምኛኛ 0.74 ከመቶ፣ አርጎብኛ 0.4 ከመቶ እንዲሁም ወላይትኛ 0.26 ከመቶ በክልሉ የሚነገሩ ቋንቋዎቸ ናቸው፡፡

ዋነኛ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎች

 

በአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ከሚገኘው ህዝብ 90 ከመቶ የሚሆነው ህዝብ አርብቶ አደር ሲሆን፤ ግመሎችን፣ የቀንድ ከብቶችን፣ ፍየልና በግ እንዲሁም አህያዎችን ያረባል፡፡ በክልሉ በቆሎ፣ ባቄላ፣ ማሽላ፣ ፓፓዬ፣ ሙዝ እና ብርቱካን በስፋት ይመረታሉ፡፡ በጥጥ ምርትም ክልሉ ያታወቃል፡፡  የንግድ እንቅስቃሴ በተለይም የጨው ማውጣት ስራ በክልሉ በስፋት ይከናወናል፡፡

 

የመሬት አቀማመጥ እና የአየር ንብረት

 

የአፋር ክልል ሙሉ ለሙሉ በስምጥ - ሸለቆ ውስጥ የሚገኝ ቦታ ነው፡፡ አብዛኛው የክልሉ ቦታዎች ጠፍጣፋ መሬት ነው፡፡ የክልሉ የከፍታ መጠን ከ160 ሜትር ከባህር ጠለል በታች (እስከ 50 oc የሚደርስ በምድር ላይ ክተኛው የሙቀት መጠን የሚመዘገብበት) እስከ 1600 ሜትር ከባህር ጠለል በላይ ይደርሳል፡፡ የክልሉ ዝቅተኛ ቦታዎች ከባህር ጠለል በላይ ከ1600 ሜትር በታች ሲሆኑ እነደ ሙሳ-አሌ ተራራ ያሉ ከፍተኛ ቦታዎች ከባህር ጠለል በላይ 2063 ሜትር ከፍታ ላይ ይገኛሉ፡፡ የአፋር ክልል የሙቀት መጠን ከ25 oc በዝናባማ ወቅት(ከመስከረም - መጋቢት) እሰከ 48 oc በደረቃማ ወቅት(ከመጋቢት - መስከረም) ይደርሳል፡፡ ላለፉት 11 ዓመታት በዱብቲ ከተማ በሚገኘው የሜትሪዎሎጂ ጣቢያ የተመዘገበው የዝናብ መጠን 187.9 ሚ.ሜ ነበር፡፡

 

ወንዞችና ሀይቆች

 

የሚሌ እና የሎጊያ ወንዞች የሚገብሩለት የአዋሽ ወንዝ ክልሉን አቋርጦ ያልፋል፡፡ የአቢ ቢል፣ የአፋምቦ እና የአብዴል ሀይቆች የአዋሽ ወንዝ የሀገሪቱን አብዛኛው ቦታዎች አዳርሶ የሚያርፍበት መዳረሻዎች ናቸው፡፡ በውስጣቸውም የተለያዩ የብዝሀ ሕይወት ስብጥርን የያዙ ናቸው፡፡

 

ማዕድን

 

በአፋር ክልል ውስጥ እንደ ጨው፣ ፖታሽ፣ ድኝ፣ ማንጋኔዝ፣ ቤንቶኔት፣ እብነ በረድ፣ የኖራ ድንጋይ እና ፔትሮሊየም ዋና ዋና ማእድናት ይገኛሉ፡፡ የተንዳሆ የከርሰምድር ሀይል ማመንጫ ለኤሌሪክ ማመነጫነት ከፍተኛ አገልግሎት የመስጠት አቅም አለው፡፡

 

ቱሪዝም እና ቅርሶች

 

የአዋሽ ጥብቅ የተፈጥሮ ደን፣ የያንጉዲ ራሳ ብሄራዊ ፓርክ እና በምድር ዝቅተኛ ቦ የሆነውየዳሎል ዝቅተኛ ቦታ እነዚህ ሁሉ በኢትዮጵያ በረሃማ ውበቶች መገለጫዎች ናቸው፡፡ በነዚህ ፓርኮች ከሚገኙ የዱር እንስሳት መካከል የአቢሲንያ የሜዳ አህያ፣ አዞ፣ አንበሳ፣ ድኩላ፣ የበርሀ ተኩላ፣ የዱር ድመት፣ አቦሸማኔ ና ሚዳቆ ይገኙበታል፡፡ ከዚህ ሁሉ ባሻገር ይህ ክልል 4.4 ሚሊዮን አመት ያለው የሰው ልጅ ቅሪተ አካል መገኛ ነው፡፡

 

ኢንቨስትመንት

 

እስከ 1998 አ.ም ድረስ 551.2 ሚሊዮን ብር ካፒታል ያስመዘገቡ 81 የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች በክልሉ ተመዝግበዋል፡፡ እነዚህም ፕሮጀክቶች ለ305,947 ዜጎች የስራ እድልን የሚፈጥሩ ናቸው፡፡ በግብርና፣ በአነስተኛ ኢንዱስትሪ፣ በግንባታ እና በአገልግሎት መስጠት ለሚሰማሩ ባለሀብቶች ፈቃድ ተሰጥቷል፡፡

 

©የቅጂ መብት 2003 የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት
የግላዊ ጉዳይ ጥበቃ ፖሊሲ |  የአጠቃቀም ደንቦች |  ኃላፊነትን ስለመወሰን | 
ተደራሽነት |  የደንበኞች ቻርተር