National Embelem of Federal Democratic Republic of Ethiopia Official Portal of Ministry of Foreign Affairs of Ethiopia
Home Page Citizen Page Government Page Diaspora Page International Community Page
 
EGov > አማርኛ > የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር > አገልግሎቶች > አዲስ ፓስፖርት ለማውጣት/ለሚስዮን መሪ

 አገልግሎቶቸ

 ቅጾቸ

 ሰነዶች

 አዲስ ፓስፖርት ለማውጣት/ለሚስዮን መሪ

አገልግሎቱን ለማግኘት መሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች 

·         የተሟላ የአዲስ ፓስፖርት ቅጽ

·         የቅርብ ጊዜ ሶስት ፎቶ ግራፍ

·         በማናቸውም ጊዜ የኢትዮጵያ ፓስፖርት ያላወጣ ከሆነ፣ ከኢትዮጵያ ያለ ጉዞ ሠነድ የወጣ መሆኑን የሚያሳይ ቅጽ

·         ግለሠቡ የሚኖርበት አገር ዜግነት ያልወሰደ መሆኑን የሚያሣይ መረጃ ከዴንማርክ /folkeregisteret/, ከስዊድን /Personbevis/, ከኖርዌይ /Folkeregister/, ከፊንላንድ /Folkeregister/,  ከአይስላንድ /Einstaklingar/,

·         ህጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ የሌለው ከሚኖርበት አገር ኢሚግሬሽን ወይም ከፖሊስ የተሰጠው የማንነት መግለጫ

·         የከፍተኛ ትምህርት በመከታተል ላይ የሚገኝ ትምህርቱን ከሚከታተልበት ተቋም የቅርብ ጊዜ ደብዳቤ

·         በቤተሰብ ግንኙነት /በስራ /በጉብኝት ወዘተ ላይ ያለ ከሆነ ይህንን የሚገልጽ መረጃ

·         ካለቀ/ከጥቅም ውጭ ለሆነ አዲስ የፓስፖርት ጥያቄ አሮጌው/ከጥቅም ውጭ የሆነው ፓስፖርት ተያይዞ መቅረብ

·         በጠፋ ፓስፖርት ምትክ የሚጠየቅ ፓስፖርቱ ለመጥፋቱ የፖሊስ መረጃ 

አገልግሎቱን ለማግኘት የሚካሄዱ ሂደቶች

1.    ማቅረብ የሚገባውን ሠነድ ለቆንስላው ሀላፊ ያቀርባል

2.    ተመዝግቦ እንዲቀርብ ለገንዘብ ያዥ ይላካል

3.    ገንዘብ ያዥ ሠነዶቹን አመሣክሮ ይመዘግብለታል

4.    የቆንስላ ሀላፊ መመዝገቡን አረጋግጦ ለሪሴኘሽኒስት ይመራል

5.    በአዲስ ፓስፖርት ላይ አስፈላጊ ጽሁፎችን በጥንቃቄ ማስፈር

6.    ትክክለኛነቱ ይረጋገጣል

7.    ሒሣብ ክፍል በመሄድ የአገልግሎት ማስፈፀሚያ ሠነድ ይዘጋጅለታል

8.    በሠነዱ ላይ የተገለፀውን የሒሣብ መጠን በዕዛው ክፍል ይከፍላል

9.    የከፈለበትን ደረሰኝ ለቆንስላው ሀላፊ ያቀርባል

10. መክፈሉ ይረጋገጣል

11. ባለጉዳዩ በአካል የቀረበ ከሆነ ሪሴኘሽኒስት ክፍል በመሄድ ይወስዳል

12. በፖስታ ቤት ከሆነ በገንዘብ ያዥ በኩል ይላክለታል

 

 የአጠቃቀም ደንቦች |  ኃላፊነትን ስለመወሰን |   Download Ge'ez Fonts
©የቅጂ መብት 2001 በኢፌዴሪ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር