አገልግሎቱን ለማግኘት መሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች
· አንድ የቅርብ ጊዜ ፎቶ ግራፍ
· የተሟላ የቪዛ መጠየቂያ ፎርም
· ቢያንስ የ6 ወር ጊዜ ግልጋሎት ያለው ፓስፖርት
· ለኢንቨስትመንት ለስራ ቅጥር፣ ለጥናትና ምርምር፣ ለመገናኛ ብዙሀን፣ ለበጎ አድራጎት ሥራ፣ ስልጠና ለመስጠት …. ወዘተ መሆኑን የሚያሳይ መረጃ
አገልግሎቱን ለማግኘት የሚካሄዱ ሂደቶች
1. ሪሴኘሽኒስት ክፍል በመሄድ የቪዛ ፎርም ማቅረብ
2. ትክክለኛነቱ ይረጋገጣል
3. የሚፈቀድላቸውን የመቆያ ጊዜ የአገልግሎቱን ቀን በፎርሙ ላይ የቆንስላ ሀላፊ ይሞላሉ
4. ሪሴኘሽኒስት ክፍል በመሄድ የተሞላውን ፎርም ያቀርባል
5. ትክክለኛነቱ ይረጋገጣል
6. ሒሣብ ክፍል በመሄድ የአገልግሎት ማስፈፀሚያ ሠነድ ይዘጋጅለታል
7. በሠነዱ ላይ የተገለፀውን የሂሣብ መጠን በዕዛው ክፍል ይከፍላል
8. የከፈለበትን ደረሠኝ ለቆንስላው ሀላፊ ያቀርባል
9. መክፈሉ ይረጋገጣል
10. ባለጉዳዩ በአካል የቀረበ ከሆነ ሪሴኘሽኒስት ክፍል በመሄድ ይወስዳል
11. በፖስታ ቤት ከሆነ በገንዘብ ያዥ በኩል ይላክለታል