በዚህ የኢትዮጵያ መንግስት ፖርታል ላይ የተለያዩ ዓይነት መረጃ፣ ቅፆች እና ልዩ ልዩ መንግስት ሰነዶች ተካተዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ፖርታሉ ከመንግስተና ከዜጎች ጋር የተሳትፎና የግንኙነት መድረኮችን አካትቷል፡፡ ፖርታሉ በዋነኛነት የሚከተሉትን ክፍሎች ይዟል፡-
· የተጠቃሚዎች መምረጫ ገፆች፡- በነዚህ ገፆች ላይ ተለይተው ለታወቁ የፖርታሉ ተገልጋዮች የተመረጡ መረጃዎች፣ አገልግሎቶች፣ ቅፆችና ሰነዶች የሚገኙበት ነው፡፡
· ስለ መንግስት፡- በዚህ ዝርዝር ስር የኢትዮጵያ መንግስትን የሚመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎችን ያገኛሉ፡፡
· ስለ ኢትዮጵያ፡- በዚህ ዝርዝር ስር ኢትዮጵያን የተመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎች ያገኛሉ፡፡
· አገልግሎቶች፡- ይህ ገፅ በተለያዩ የሚኒስቴር መ/ቤቶች ወደሚሰጡ አገልግሎቶች ዝርዝር ይወስድዎታል፡፡ ተገልጋዮች አገልግሎቶቹን ለማግኘት የሚያስፈልጓቸውን ሰነዶችና ቀደም ተከተሎች የዘረዝራል፡፡
· ቅፆች፡- ይህ ገጽ የተለያዩ የመንግስት መ/ቤቶች ለአገልግሎት መስጫ የሚጠቀሙባቸውን ቅፆች አውርዶ ለመጠቀም ያስችላል፡፡
· ሰነዶች፡- ይህ ገፅ የተለያዩ የመንግስት መ/ቤቶች የሚገለገሉባቸውን ሰነዶች የያዘ ነው፡፡
· ይሳተፉ፡- ይህ ገጽ የፖርታሉ ተገልጋዮች በመንግስት ጉዳዮች ላይ ተሳትፎ ወደሚያደርጉበት ገፅ የሚወስድ ነው፡፡ በዚህ ክፍልም የውይይት መደረኮች፣ ዳሰሳዎች፣ ብሎጎችና ሌሎችንም አሳታፊ ገፅታዎችን ያገኛሉ፡፡
· የመንግስት ዜናዎች፡- ይህ ገጽ የተለያዩ ወቀታዊ የሆኑ ዜናዎችንና ለውጦችን የያዘ ነው፡፡
· የዜጎች የህይወት ክንውኖች፡- አገልግሎቶችን በርዕስ ተከፋፍለው የተቀመጡበት ሲሆን ዜጎች በእለት ተእለት የሚፈልጉአቸው አገልግሎቶችን ያካተተ ነው፡፡
· ለመንግስት፣ ለነጋዴዎች፣ ለውጭ ዜጎችና ለመያድ፡- በነዚህ ክፍልፋይ የተመረጡ አገልግሎቶችን በተጠቃሚው ዓይነት የሚገኙበት ነው፡፡
· ፍለጋ፡- በፖርታሉ ላይ የሚገኙ ማንኛውንም ዓይነት መረጃ ለመፈለግ ያችላል፡፡