Embelem of Federal Democratic Republic of Ethiopia Official Portal of Federal  Democratic Republic of Ethiopia  
Home Home Citizens Citizens Government Government Businesses Businesses Forigners Forigners NGOs NGOs Decrease font Increase font
 

 የግለኝነት መብት ፖሊሲ

ጥረታችን/ኃላፊነታችን

የኢትዮጵያ መንግስት በዚህ ፖርታል ላይ በሚደረግ የመረጃ ቅብብል ወቅት ለሚሰጡት የግል መረጃ በጥንቃቄ ይይዛል፡፡ ጥንቃቄ የሚያስፈልጋቸውን የግል መረጃዎትን የመጠበቅ ኃለፊነታችንን በመገንዘብም ይህንን የግለኝነት መብት ፖሊሲና ደህንነት ገፅ አዘጋጅተናል፡፡ ይህንን ፖርታል ለጉብኝት ወይም ለኤሌክትሮኒክ-ግብይት በሚጠቀሙበት ወቅት ለሚሰጡት የግል መረጃ ተገቢውን ጥበቃ ለማድረግ የላቀ ጥረት እናደርጋለን፡፡

መረጃዎትን መውሰድና መጠቀም

ድህረ ገፃችን በሚጎበኙበት ወቅት፤ አገልግሎቱን ለማግኘት ከሚጠየቁ መረጃዎች በስተቀር የግል መረጃዎትን እንዲሰጡ አንጠይቅም፡፡

የአይ.ፒ አድራሻ መውሰድ

የመረጃ ድረ-ገፃችን በሚጎበኙበት ቅፅበት የድረ-ገፅ ሰርቨራችን የእርስዎን አይ.ፒ አድራሻ ይሰበስባል (የእርስዎ የአይ.ፒ አድራሻ የኮምፒውተርዎት ልዩ መለያ ሲሆን ኢንተርኔት ላይ የሚገኙ ሌሎች ኮምፒውተሮች ለእርስዎ መረጃ የሚልኩበት አድራሻ ነው፡፡) የእርስዎን የአይ.ፒ አድራሻ ከሰርቨራችን በኩል ለሚከሰቱ ችግሮች ለመፍታትና የድረ-ገፃችንን የተጠቃሚ ብዛት መረጃ ለማጠናቀር እንጠቀምበታለን፡፡

ለግል መረጃዎት የሚደረግ ጥበቃ

የግል መረጃዎት እንዲያውቁት ከሚፈለግ የመንግስት ሰራተኞች በስተቀር ለማንም ግልፅ አይደረግም፡፡

©የቅጂ መብት 2003 የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት
የግላዊ ጉዳይ ጥበቃ ፖሊሲ |  የአጠቃቀም ደንቦች |  ኃላፊነትን ስለመወሰን | 
ተደራሽነት |  የደንበኞች ቻርተር