አገልግሎቱን ለማግኘት የሚያስፈልጉ መስፈርቶች
- በህግ አግባብ የተዘጋጀ የውል ፅሁፍ /ፎርም/
- የባቤትነት መታወቂያ /ሊብሬ/
- ከትራንስፖርት ባስልጣን የዋጋ ግምት ማስረጃ እና ክሊራንስ
- አግባብ ካለው ግብር አስከፋይ መስሪያ ቤት ክሊራንስ
አገልግሎቱ ለማግኘት የሚካሄዱ
- ባለ ጉዳዩ ሠነዱ ተረጋግጦ እንዲመዘገበለት ጥያቄ ያቀርባል
- ስምሪትና መስተንግዶ ሠራተኛ አመጣጥኖ ያሠማራል
- የሥራ ክፍሉ ሀላፊ ለህግና ለሞራል የማይቃረን መሆኑን ይመረምራል
- አጣሪና አፈራራሚ ሠራተኛ ያጣራል፣ ያፈራርማል፣ ይመዘግባል
- ገንዘብ ተቀባይ የአገልግሎትና የቴምብር ቀረጥ ክፍያ ይሰበስባል
- ሠነድ አረጋጋጭና መዝጋቢ ሠራተኛ ሰነዶችን በማያያዝና ማህተም በማድረግ ቁጥርና ቀን ይሰጣል
- የሥራ ክፍሉ ሀላፊ በመፈረም ቲተሩን ያስቀምጣል
- የመማህተምና ዕደላ ሠራተኛ በገጹ ላይ ማህተም በማድረግ የባለጉዳዩን ድርሻ ይሠጣል የሥራ ሂደቱን ቀሪ ሰነድ ያስተላልፋል