|
|
|
|
|
|
|
|
|
|
|
|
|
|
አገልግሎቱን ለማግኘት የሚያስፈልጉ መስፈርቶች
- በህግ አግባብ የተዘጋጀ የውል ፅሁፍ /ፎርም/
- የባለቤትነት መታወቂያ /ሊብሬ/
- ከትራንስፖርት ባለሥልጣን የዋጋ ግምት ማስረጃ እና ክሊራንስ
አገልግሎቱን ለማግኘት የሚካሄዱ ሂደቶች
- ባለ ጉዳዩ ሠነዱ ተረጋግጦ እንዲመዘገብለት ጥያቄ ያቀርባል
- ስምሪትና መስተንግዶ ሠራተኛ አመጣጥኖ ያሠማራል
- የሥራ ክፍሉ ሀላፊ ለህግና ለሞራል የማይቃረን መሆኑን ይመረመራል
- አጣሪና አፈራራሚ ሠራተኛ ያጣራል፡ ያፈራርማል፣ ይመዘግባል
- ገንዘብ ተቀባይ የአገልግሎትና የቴምብር ቀረጥ ክፍያ ያሰባስባል
- ሠነድ አረጋጋጭና መዝጋቢ ሠራተኛ ሰነዶችን በማያያዝና ማህተም በማድረግ ቁጥርና ቀን ይሰጣል
- የሥራ ክፍሉ ሀላፊ በመፈረም ቲተሩን ያስቀምጣል
- የማህተምና ዕደላ ሠራተኛ በየገፁ ላይ ማህተም በማድረግ የባለጉዳዩን ድርሻ ይሠጣል የሥራ ሂደቱን ቀሪ ሠነድ ያስተላልፋል
|
|
|
|
|
|
|
|
|