Embelem of Federal Democratic Republic of Ethiopia Official Portal of Federal  Democratic Republic of Ethiopia  
Home Home Citizens Citizens Government Government Businesses Businesses Forigners Forigners NGOs NGOs Decrease font Increase font
 

 የፊክስድ ላየን ስልክ ማውጣት-የኪራይ ቤቶች ተከራይ አገልግሎቱን ለመጠየቅ

  አገልግሎቱን ለማግኘት የሚያስፈልጉ መስፈርቶች 
  • የቀበሌ ነዋሪነት መታወቂያ
  • አገልግሎቱን ጠያቂው ግለሠብ ከኪራይ ቤቶች አስተዳደር ቤቱን ለመያዙ/ለመከራየቱ ህጋዊ የኪራይ ውል ማስረጃ ሲያቀርብ
  • ከላይ የተጠቀሱትን አገልግሎት ለማግኘት ጠያቂዎች ከዚህ በታች ያሉትን አንዱን ማሟላት አለባቸው

 o       በራሱ ስም ተመዝግቦ የሚገኝ ግምቱ ከ15.000 ብር የማያንስ ተንቀሳቃሽ ወይም ቋሚ ንብረት ሲያቀርብ

 o       የኮርፖሬሽኑ ደንበኛ የሆነ ግለሰብ በዋስትና ሰጪነት ሲቀርብና ዋሱም እዳ ሲኖር ለመክፈል ፈቃደኛ መሆኑን በጽሁፍ ሲያረጋግጥ

 o       እውቅና ካለው ትልቅ የግል ድርጅት ወይም የመንግስት መ/ቤት ውስጥ በሚሠራ ሠራተኛ ዋስትና ሰጪነት

 o       ግምቱ ከ15.000 ብር የማያንስ ቋሚ ወይም ተንቀሳቃሽ ንብረት ያለው ግለሰብ ዋስትና ሰጪ ከማንኛውም መታወቂያ  ጋር     ሲቀርብ መስተናገድ ይቻላል 

      አገልግሎቱን ለማግኘት የሚከናወኑ ሂደቶች 

  1. የሽያጭ ማዕከል ቢሮ በመሄድ ማመልከቻ ያቀርባል

  2. የሽያጭ ማዕከል ቢሮ ማመልከቻውን ይመለከታል

  3. የሽያጭ ማዕከል ቢሮ ማመልከቻውን ከመረመረ በኃላ ወደ ኢንስታሌሽን ክፍል ይላካል

  4. ኢንስታሌሽን ክፍል በደንበኛው አካባቢ ክፍት መስመር እንዳለ ይመለከታል

  5. የሽያጭ ማዕከል ቢሮ በመሄድ የአገልግሎት ክፍያ ይከፍላል

  6. የከፈለበትን ደረሰኝ ኢንስታሌሽን ክፍል ያቀርባል

  7. በዛው ቢሮ ቀነ ቀጠሮ ይሠጠዋል

  8. የፊክስድ ላየን ስልክ ቀፎ በመግዛት ቤቱ ይጠብቃል

  9. መስመሩ ከተገኘ በኋላ ቤቱ በመሄድ መስመር ይዘረጋል

©የቅጂ መብት 2003 የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት
የግላዊ ጉዳይ ጥበቃ ፖሊሲ |  የአጠቃቀም ደንቦች |  ኃላፊነትን ስለመወሰን | 
ተደራሽነት |  የደንበኞች ቻርተር