አገልግሎቱን ለማግኘት የሚያስፈልጉ መስፈርቶች
- በሕግ አግባብ የተዘጋጀ የውክልና ስልጣን መስጫ ሠነድ
- በውክልና ማስረጃው ላይ የተጠቀሰ የተለየ ንብረት ወይም መብት ካለ የወካይ መሆኑን የሚያረጋግጥ ማስረጃ
አገልግሎቱን ለማግኘት የሚከናወኑ ሂደቶች
-
ባለ ጉዳዩ ሠነዱ ተረጋግጦ እንዲመዘገብለት ጥያቄ ያቀርባል
-
ስምሪትና መስተንግዶ ሠራተኛ አመጣጥኖ ያሠማራል
-
የስራ ክፍሉ ኃላፊ ለሕግና ለሞራል የማይቃረን መሆኑን ይመረምራል
-
አጣሪና አፈራራሚ ሠራተኛ ያጣራል፣ያፈራርማል፣ይመዘግባል
-
ገንዘብ ተቀባይ የአገልግሎትና የቴምብር ቀረጥ ክፍያ ይሰበስባል
-
ሠነድ አረጋጋጭና መዝጋቢ ሠራተኛ ሰነዶችን በማያያዝና ማህተም በማድረግ ቁጥርና ቀን ይሰጣል
-
የስራ ክፍሉ ኃላፊ በመፈረም ቲተሩን ያስቀምጣል
-
የማህተምና የዕደላ ሠራተኛ በየገፁ ላይ ማህተም በማድረግ የባለ ጉዳዩን ድርሻ ይሠጣል የሥራ ሂደቱን ቀሪ ሰነድም ያስተላልፋል