Embelem of Federal Democratic Republic of Ethiopia Official Portal of Federal  Democratic Republic of Ethiopia  
Home Home Citizens Citizens Government Government Businesses Businesses Forigners Forigners NGOs NGOs Decrease font Increase font
 

 አዲስ መንጃ ፈቃድ ማውጣት

        

  የመንጃ ፈቃድ አይነቶች

1. ሞተር ሳይክል

2. አውቶ ሞቢል

3. ታክሲ 1

4. ታክሲ 2

5. የህዝብ 1

6. የህዝብ 2

7. ደረቅ ጭነት 1

8. ደረቅ ጭነት 2

9. ደረቅ ጭነት 3

10.  ፍሳሽ 1

11.  ፍሳሽ 2

አገልግሎት ላይ ያሉ የመ.ፈ.አይነቶች

የጽሁፍ ስልጠና ሰዓት

የተግባር /የመኪና/ስልጠና

የአገልግሎቶቹ ክፍያ

የትምህርት ደረጃ

ዕድሜ

አውቶ ሞቢል

54.50

30 ሰዓት

2365

4ኛ ክፍልና በላይ

18 ዓመትና በላይ

ደረቅ ጭነት 1

60.50

35 ሰዓት

3075

8ኛ ክፍልና በላይ

21 ዓመትና በላይ

ደረቅ ጭነት 2

60.50

50 ሰዓት

5375

8ኛ ክፍልና በላይ

24 ዓመትና በላይ

ደረቅ ጭነት 3

60.50

65 ሰዓት

8428

8ኛ ክፍልና በላይ

24 ዓመትና በላይ

ታክሲ 2

79.50

30 ሰዓት

2735

8ኛ ክፍልና በላይ

25 ዓመትና በላይ

የህዝብ 1

79.50

45 ሰዓት

3935

8ኛ ክፍልና በላይ

24 ዓመትና በላይ

 አገልግሎትን ለማግኘት የሚያስፈልጉ መስፈርቶች

·   የቀበሌ ነዋሪነት ማረጋገጫ መታወቂያ

·   4 ጉርድ ፎቶ ግራፍ 

·   የትምህርት ማስረጃ

አገልግሎቱን ለማግኘት የሚከናወኑ ሂደቶች

1.   በመንገድ ትራንስፖርት እውቅና በተሠጣቸው የመንጃ ፈቃድ ስልጠና የሚሠጡ ትምህርት ቤቶች በመሄድ መመዝገብ

2.   በትምህርት ቤቱ ሲመዘገቡ የሜዲካል ምርመራ ከጤና ጣቢያ እንዲያመጡ ደብዳቤ ይሠጣቸዋል

3.   የተሠጣቸውን ደብዳቤ በመያዝ ጤና ጣቢያ የሜዲካል ምርመራ ማከናወን

4.   የተመረመሩበትን ውጤት በተመዘገቡበት ት/ቤት በቀጠሮ ቀን ማቅረብ ማውጣት

5.   በሚፈልጉት የመንጃ ፈቃድ አይነት በተሠጣቸው ሰዓት መሠረት የጽሁፍ /የንድፈ ሀሳብ/  ስልጠና ማከናወን

6.     የጽሁፍ /የንድፈ ሀሳብ/ ስልጠናውን ከጨረሱ በኋላ የተግባር /የመኪና/ ትምህርት እንዲወስዱ ቃሊቲ በትምህርት ቤቱ መኪና እንደ ሰዓቱ በቀን ለአንድ ሰዓት ስልጠና ይሠጣል

7.     የተግባር ስልጠናው ካለቀ በኋላ ቃሊቲ በሚገኘው መንገድ ትራንስፖርት የፈተና ማስቀጠሪያ ደብዳቤ ይሠጣቸዋል

8.     የተሠጣቸውን ደብዳቤ ለቃሊቲ መንገድ ትራንስፖርት የፈተና መስጪያ ቢሮ ያቀርባሉ

9.     በደብዳቤው መሠረት የፈተና ቀን ቀጠሮ ይሠጣቸዋል

10.  በቀጠሮ ቀን በመሄድ የቃል /የጽሁፍ/ እና የተግባር /የመኪና/ ጠዋትና ከሠአት ፈተና ይፈተናሉ

11.  የፈተናውን ውጤት በዛው እለት እንዲያውቁ ይደረጋል

12.  በፈተና መስጪያ ቢሮ 2 ጉርድ ፎቶ ግራፍ ያቀርባሉ

13.  በዛው ቢሮ የ5 ብር ቴምብር ገዝተው ያቀርባሉ

14.  የአገልግሎትና የመንጃ ፈቃድ ደብተር ክፍያ በገንዘብ ቤት ይከፍላሉ

15.  የተከፈለበትን ደረሠኝ በፈተና መስጪያ ቢሮ ያስገባሉ

16.  በክፍለ ከተማቸው በሚገኝ የመንገድ ትራንስፖርት ቅርንጫፍ ጽ/ቤት መንጃ ፈቃዱን እንዲወስዱ ቀጠሮ ይሠጣቸዋል

17.  በቀጠሮ ቀን በክፍለ ከተማው ትራንስፖርት ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በመሄድ መንጃ ፈቃዱን ይወስዳሉ  

©የቅጂ መብት 2003 የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት
የግላዊ ጉዳይ ጥበቃ ፖሊሲ |  የአጠቃቀም ደንቦች |  ኃላፊነትን ስለመወሰን | 
ተደራሽነት |  የደንበኞች ቻርተር