አገልግሎቱን ለማግኘት መሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች
- ኢትዮጵያዊ ከሆነ ማንነቱን የሚገልፅ መታወቂያ ከ3 ኮፒ ጋር
- ኢትዮጵያዊ ካልሆነ ፓስፖርት ከ3 ኮፒ ጋር
- 3 ፓስፖርት ሳይዝ ጉርድ ፎቶግራፎች
- 3 ፎልደሮች /ፋይሎች/
- በውክልና ከሆነ ሕጋዊ የውክልና ወረቀት
- በማህበር ከሆነ የመመስረቻ ጽሁፍ የመተዳደሪያ ደንብ
አገልግሎቱን ለማግኘት የሚከናወኑ ሂደቶች
-
ኢንፎርሜሽን ዴስክ በመሄድ ወደሚመለከተው ክፍል ይመራል
-
ፕሮሞሽን ቢሮ በቂ ኢንፎርሜሽን ይሠጠዋል
-
ወደ ኢንፎርሜሽን ዴስክ ተመልሶ አዲስ የኢንቨስትመንት ፈቃድ ለማግኘት የሚሞላውን ቅጽ ይሞላል
-
ወደ ፈቃድና ምዝገባ ክፍል በመሄድ የሞላውን ፎርም በ3 ኮፒ ይሠጣል
-
እዛው ቢሮ ትክክለኝነቱ ይረጋግጣል
-
ወደ ሂሳብ ክፍል በመውሰድ የአገልግሎት ክፍያ ማስፈፀሚያ ሰነድ ይዘጋጃል
-
በሂሳብ መክፈያ ሰነድ ላይ የተገለፀውን የገንዘብ መጠን ተጠቃሚው በዛው ቢሮ ይከፍላል
-
መክፈሉ ከተረጋገጠ በኋላ ለፈቃድና ምዝገባ ክፍል ደብዳቤ ይጻፍለታል
-
የፈቃድና ምዝገባ ኃላፊ ይፈርሙበታል
-
በመጨረሻም ከመዝገብ ቤት ሕጋዊነቱን የሚገልጽ ማህተም ከተደረገ በኋላ ድርሻውን ለባለጉዳዩ ይሠጣል