የመንግስት አገልግሎት ቅድመ ሁኔታዎች የመንግስት አገልግሎት ቅድመ ሁኔታዎችየመንግስት አገልግሎቶች የመንግስት አገልግሎቶች

Back

አዲስ የኢንቨስትመንት ፈቃድ

አገልግሎቱን ለማግኘት መሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች

 • ኢትዮጵያዊ ከሆነ ማንነቱን የሚገልፅ መታወቂያ ከ3 ኮፒ ጋር
 • ኢትዮጵያዊ ካልሆነ ፓስፖርት ከ3 ኮፒ ጋር
 • 3 ፓስፖርት ሳይዝ ጉርድ ፎቶግራፎች
 • 3 ፎልደሮች /ፋይሎች/ 
 • በውክልና ከሆነ ሕጋዊ የውክልና ወረቀት
 • በማህበር ከሆነ የመመስረቻ ጽሁፍ የመተዳደሪያ ደንብ

አገልግሎቱን ለማግኘት የሚከናወኑ ሂደቶች

 1. ኢንፎርሜሽን ዴስክ በመሄድ ወደሚመለከተው ክፍል ይመራል
 2. ፕሮሞሽን ቢሮ በቂ ኢንፎርሜሽን ይሠጠዋል
 3. ወደ ኢንፎርሜሽን ዴስክ ተመልሶ አዲስ የኢንቨስትመንት ፈቃድ ለማግኘት የሚሞላውን ቅጽ ይሞላል
 4. ወደ ፈቃድና ምዝገባ ክፍል በመሄድ የሞላውን ፎርም በ3 ኮፒ ይሠጣል
 5. እዛው ቢሮ ትክክለኝነቱ ይረጋግጣል
 6. ወደ ሂሳብ ክፍል በመውሰድ የአገልግሎት ክፍያ ማስፈፀሚያ ሰነድ ይዘጋጃል
 7. በሂሳብ መክፈያ ሰነድ ላይ የተገለፀውን የገንዘብ መጠን ተጠቃሚው በዛው ቢሮ ይከፍላል
 8. መክፈሉ ከተረጋገጠ በኋላ ለፈቃድና ምዝገባ ክፍል ደብዳቤ ይጻፍለታል
 9. የፈቃድና ምዝገባ ኃላፊ ይፈርሙበታል
 10. በመጨረሻም ከመዝገብ ቤት ሕጋዊነቱን የሚገልጽ ማህተም ከተደረገ በኋላ ድርሻውን ለባለጉዳዩ ይሠጣል