የመንግስት አገልግሎት ቅድመ ሁኔታዎች የመንግስት አገልግሎት ቅድመ ሁኔታዎችየመንግስት አገልግሎቶች የመንግስት አገልግሎቶች

Back

ለጥቃቅንና አነስተኛ ንግድ ብድር

አገልግሎቱን ለማግኘት የሚያስፈልጉ መስፈርቶች

 • እድሜያቸው ከ18 ዓመት በላይ የሆኑ
 • የቀበሌው ነዋሪነት መሆናቸው ማረጋገጫ ወይም የቀበሌ መታወቂያ
 • ስነ ምግባራቸው የተመሠከረላቸው 
 • በግል በማህበር እና በቡድን ተቧድነው መበደር የሚፈልጉ
 • መስራት የሚችሉ የአካል ጉዳተኞች 
 • ከሌሎች አበዳሪዎች ብድር የሌለባቸው መሆን አለበት

አገልግሎቱን ለማግኘት የሚከናወኑ ሂደቶች

 1. ከዚ በላይ የተጠቀሱትን ካሟሉ በኋላ ሁለት ጉርድ ፎቶ ግራፍ 
 2. የማመልከቻ ደብዳቤ አዲስ ብድርና ቁጠባ ቢሮ ያስገባሉ 
 3. የሚመለከተው አካል ማመልከቻውን ተመልክቶ ሁኔታውን ይመረምራል
 4. የሚሠሩበትን ቦታ ለቢሮው አባል ወስደው ያሣያሉ
 5. ከዚ በፊት ብድር ወስደው ከሆነ በተገቢው ጊዜ ከፍለው ያጠናቀቁ መሆኑን ማረጋገጫ ደብዳቤ
 6. አዲስ ብድርና ቁጠባ ቢሮ ሀላፊ ጉዳዩን ከመረመረ በኋላ ብድሩን ያፀድቃል
 7. ለተበዳሪው አባላት ሁለትና ከሁለት ቀን በላይ ስልጠና ይሰጣል
 8. የብድሩ ክፍያ ሁኔታ፡-በራስ ፍቃድና፣ በስምምነት በየወሩ ይከፍላሉ