የመንግስት አገልግሎት ቅድመ ሁኔታዎች የመንግስት አገልግሎት ቅድመ ሁኔታዎችየመንግስት አገልግሎቶች የመንግስት አገልግሎቶች

Back

ኮንዶሚኒየም ቤት ዕጣ ለወጣላቸው ባለዕድለኞች

አገልግሎቱን ለማግኘት መሟላት የሚገባቸው መሥፈርቶች

 • የምዝገባ ቢጫ ካርድ
 • የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ ዋናውንና ፎቶ ኮፒ
 • የተለያዩ ክፍያዎች ለባንክ የከፈሉበት ደረሰኝ
 • በቀበሌ የተሞላ  ቅጽ/9/ /የነበረውን ቤት ለአከራይ እንዲያስረክቡ የመተማመኛ/
 • መረጃዎችን አሟልተው ሲቀርቡ የቤት ሽያጭ ውል ይዋዋላሉ
 • የጋብቻ ምስክር ወረቀት ዋናውንና ፎቶ ኮፒ
 • ያላገቡ ከሆነ ከሚኖሩበት ቀበሌ ማረጋገጫ ማቅረብ

አገልግሎቱን ለማግኘት የሚከናወኑ ሂደቶች

 1. የቤቶች ማስተላለፍና ማስተዳደር ክፍል በመሄድ ማቅረብ የሚገባቸውን ሰነዶች ያቀርባሉ
 2. ትክክለኛነቱ ይረጋገጣል
 3. የኮንዶሚኒየም ቤት የመግዛት ዕድል የሚሰጣቸው የቅድሚያ ወይም ሙሉ ክፍያ እንዲፈጽሙና ከባንክ ጋር የብድር ውለታ እንዲፈጽሙ የማሳወቂያ ቅጽ ይሞላሉ
 4. ፎርም በትክክል መሞላቱ ይረጋገጣል
 5. በእዛው ክፍል የአገልግሎት ማስፈፀሚያ ሠነድ ይዘጋጅለታል
 6. በሂሳብ ሠነድ ላይ የተገለፀውን የሂሳብ መጠን በዛው ክፍል ይከፍላል
 7. መክፈሉ ይረጋገጣል
 8. የቤት ሽያጭ ውል ይፈራረማሉ
 9. በመጨረሻም ሕጋዊ የሆነ የቤት ሽያጭ ውል ሠርተፍኬት ይሠጣል