የመንግስት አገልግሎት ቅድመ ሁኔታዎች የመንግስት አገልግሎት ቅድመ ሁኔታዎችየመንግስት አገልግሎቶች የመንግስት አገልግሎቶች

Back

የንግድ ማህበራት የመመስረቻ ጽሁፍና መተዳደሪያ ደንብ ማጽደቅ

አገልግሎቱን ለማግኘት የሚያስልጉ መስፈርቶች

 • በሕጉ በአግባብ የተዘጋጀ የመመሥረቻ ጽሁፍና የመተዳደሪያ ደንብ
 • የስም ስያሜውን የሚያመለክት ማስረጃ ከንግድና ኢንዱስትሪ ሚ/ር
 • ማህበሩ ባንክን፣ ኢንሹራንስን ወይም ሌሎች የገንዘብ ተቋማትን የሚመለከት ከሆነ በኢትዮåያ ብሔራዊ ባንክ በሽኝ ደብዳቤ የተላከ ማህተም ያረፈበት የመመሥረቻ ጽሁፍና የመተዳደሪያ ደንብ ረቂቅ
 • በሰነዱ ላይ የተጠቀሰ የዓይነት መዋà ካለ የንብረቱ የባለቤትነት ማረጋገጫ ሰነድ፣ንብረት የማይንቀሳቀስ ንብረት ከሆነ የጋብቻ ማስረጃ፣ ጋብቻ ከሌለ ይህንን የሚያረጋግጥ የቀበሌ ወይም የማዘጋጃ ቤት ማስረጃ
 • በሰነዱ ላይ ለአካለ መጠን ያልደረሰ አባል ካለ የልደት ምስክር ወረቀት ወይም የፍርድ ቤት ማስረጃ

አገልግሎቱን ለማግኘት የሚካሄዱ ሂደቶች

 1. ባለ ጉዳዩ ሠነዱ ተረጋግጦ እንዲመዘገብለት ጥያቄ ያቀርባል
 2. ስምሪትና መስተንግዶ ሠራተኛ አመጣጥኖ ያሠማራል
 3. የስራ ክፍሉ ሀላፊ ለህግና ለሞራል የማይቃረን መሆኑ ይመረምራል
 4. አጣሪና አፈራራሚ ሠራተኛ ያጣራል፣ ያፈራርማል፣ ይመዘግባል
 5. ገንዘብ ተቀባይ የአገልግሎትና ቴምብር ቀረጥ ክፍያ ያሰባስባል
 6. ሠነድ አረጋጋጭ መዝጋቢ ሠራተኛ ሰነዶችን በማያያዝና ማህተም በማድረግ ቁጥርና ቀን ይሰጣል
 7. የስራ ክፍሉ ሀላፊ በመፈራረም ቲተሩን ያስቀምጣል
 8. የማህተምና የዕደላ ሠራተኛ በየገፁ ላይ ማህተም በማድረግ የባለ ጉዳዩን ድርሻ ይሰጣል የሥራ ሂደቱን ቀሪ ሠነድ ያስተላልፋል