የመንግስት አገልግሎት ቅድመ ሁኔታዎች የመንግስት አገልግሎት ቅድመ ሁኔታዎችየመንግስት አገልግሎቶች የመንግስት አገልግሎቶች

Back

ገመድ አልባ /የዋየርለስ/ ስልክ ማውጣት-የግለሠብ ቤት ተከራይተው

አገልግሎቱን ለማግኘት የሚያስፈልጉ መስፈርቶች 

  • የቀበሌ ነዋሪነት መታወቂያ
  • አከራይና ተከራይ የቤት ኪራይ ውል ወይም ቤቱ በአገልግሎት ጠያቂው መከራየቱን አከራይ የፅሁፍ ማስረጃ ሲያቀርብ
  • አከራይ ተከራይ ስልክ እንዲያስገባ ለመፍቀድ በግንባር ቀርቦ በጽሁፍ ሲያቀርብ እና በቤቱ አከራይ ስም ተመዝግቦ የሚገኝ ለመሆኑ ህጋዊ ማስረጃ ሲያቀርብ

አገልግሎቱን ለማግኘት የሚከናወኑ ሂደቶች

  1. የሽያጭ ማዕከል ቢሮ በመሄድ ማመልከቻ ያቀርባል
  2. የሽያጭ ማዕከል ቢሮ ማመልከቻውን ይመለከታል
  3. በዛው ቢሮ የአገልግሎት ክፍያ ይከፍላል
  4. በዛው ቢሮ የከፈለበትን ደረሰኝ ያቀርባል
  5. በዛው ቢሮ ቀነ ቀጠሮ ይሠጠዋል
  6. ገመድ አልባ ቀፎ በመግዛት ያስመዘግባል
  7. ክፍት አገልግሎት በሚገኝበት ጊዜ መስመሩ ይለቀቅለታል