888 ነፃ ጥሪን በመደወል 888 ነፃ ጥሪን በመደወል

የ888 ጥሪ ማዕከል በመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አማካኝነት የተቋቋመ የመንግስት ጥሪ ማዕከል ሲሆን ለደንበኞች ከክፍያ ነፃ በሆነው መስመር 888 በመደወል ከተለያዩ የመንግስት መ/ቤቶች አገልግሎቶች ጋር ተያይዞ ለሚነሱ ጥያቄዎች መረጃና መልስ መስጫ መንገድ ነው፡፡

በጥሪ ማዕከሉ አገልግሎት የሚሰጡ የፌደራል የመንግስት መ/ቤቶች
 • የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ሚኒስቴር
 • የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር
 • የከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስቴር
 • የወጣቶችና ስፖርት ሚኒሰቴር
 • የሠነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ጽ/ቤት
 • የፌደራል ጠቅላይ አቃቢ ህግ
 • የመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ
 • የብሄራዊ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መፃህፍት ኤጀንሲ
 • የፌደራል ትራንስፖርት ባለስልጣን
 • የግል ድርጅቶች ሰራተኞች ማህበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ
 • የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን
በጥሪ ማዕከሉ አገልግሎት የሚሰጡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳድር የመንግስት መ/ቤቶች
 • የአዲስአበባ ከተማ አስተዳደር የይዞታ አስተዳደር የሽግግር ግዜ አገልግሎት ጽ/ቤት
 • የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ባለስልጣን
 • የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳድር የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ
  • በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሚገኙ የመንግስት መ/ቤቶችን መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
በጥሪ ማዕከሉ አገልግሎት የሚሰጡ የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የመንግስት መ/ቤቶች
 • በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የሚገኙ የመንግስት መ/ቤቶችን መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
በጥሪ ማዕከሉ አገልግሎት የሚሰጡ የክልል የመንግስት መ/ቤቶች
 • የትግራይ ክልል
  በትግራይ ክልል የሚገኙ የመንግስት መ/ቤቶችን መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
 • የአማራ ክልል
  በአማራ ክልል የሚገኙ የመንግስት መ/ቤቶችን መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
 • የኦሮሚያ ክልል
  • የኦሮሚያ ፍትህ አካላት ዘርፍ
  • የኦሮሚያ ማህበራዊ ዘርፍ
  • የኦሮሚያ ኢንዱስተሪና ከተማ ልማት ዘርፍ
  • የኦሮሚያ እርሻና ገጠር ልማት ዘርፍ
  • የኦሮሚያ ድጋፍ ሰጪ ተቋማት
 • የደቡብ ክልል
  በደቡብ ክልል የሚገኙ የመንግስት መ/ቤቶችን መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
 • የሶማሌ ክልል
  በሶማሌ ክልል የሚገኙ የመንግስት መ/ቤቶችን መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡