Government Service Requriements Government Service RequriementsGovernment Services Government Services

Back

አዲስ የውሃ መስመር ማስቀጠል

አገልግሎት ለማግኘት የሚያስፈልጉ መስፈርቶች

  • የመኖሪያ ቤት ባለቤትነት ማረጋገጫ ካርታ
  • የቀበሌ ነዋሪነት ማረጋገጫ መታወቂያ

አገልግሎቱን ለማግኘት የሚከናወኑ Cደቶች

  1. የደንበኞች አገልግሎት መጠየቂያ ፎርም ከደንበኞች አገልግሎት ስራ ሂደት ቢሮ በመውሠድ ይሞላል 
  2. የተሞላው ፎርም በዛው ቢሮ ትክክለኝነቱ ከተረጋገጠ በኋላ የድርጅቱ ተወካይ ውሳኔ ይሰጥበታል 
  3. ለተጠየቀው አገልግሎት የሚፈለገው የዋጋ ግምት በዛው ክፍል ይከናወናል
  4. የተገመተውን የክፍያ መጠን የሚያረጋግጥ የሂሳብ ሰነድ ይዘጋጃል 
  5. በተጠቀሰው የሂሣብ መክፈያ ደረሰኝ መሠረት ክፍያው በእዛው ክፍል ይከናወናል 
  6. የተከፈለበት ደረሰኝ ወደሚመለከተው የቴክኒክ ክፍል ይመራል
  7. በተመራለት የቴክኒክ ክፍል ለተጠቀሰው አገልግሎት አስፈላጊ የሆነውን የውሀ መስመር በፐሮግራሙ መሠረት ይዘረጋል