Government Service Requriements Government Service RequriementsGovernment Services Government Services

Back

የፈቃድ ማረጋገጫ መስጠት

አገልግሎቱን ለማግኘት የሚያስልጉ መስፈርቶች

 • በሕግ አግባብ የተዘጋጀ የዲክላራሲዮን ማመልከቻ
 • የልደት የምስክር ወረቀት ወይም የጋብቻ ማስረጃ እንደአስፈላጊነቱ
 • በተለይ የተጠቀሰ ነገር ካለ ይህንኑ የሚያረጋግጥ ማሰረጃ /ለምሳሌ፣ የቤተሰብነት ማረጋገጫ ማስረጃ፣ የህክምና ማስረጃ፣ ወዘተ…./

አገልግሎቱን ለማግኘት የሚካሄዱ ሂደቶች

 1. ባለ ጉዳዩ ሠነዱ ተረጋግጦ እንዲመዘገብለት ጥያቄ ያቀርባል
 2. ስምሪትና መስተንግዶ ሠራተኛ አመጣጥኖ ያሠማራል
 3. የስራ ክፍሉ ሀላፊ ለህግና ለሞራል የማይቃረን መሆኑን ይመረምራል
 4. አጣሪና አፈራራሚ ሠራተኛ ያጣራል፣ ያፈራርማል፣ ይመዘግባል
 5. ገንዘብ ተቀባይ የአገልግሎትና ቴምብር ቀረጥ ክፍያ ያሰባስባል
 6. ሠነድ አረጋጋጭና መዝጋቢ ሠራተኛ ሰነዶችን በማያያዝና ማህተም በማድረግ ቁጥርና ቀን ይሰጣል
 7. የሥራ ክፍሉ ኃላፊ በመፈራረም ቲተሩን ያስቀምጣል
 8. የማህተምና ዕደላ ሠራተኛ በየገፁ ላይ ማህተም በማድረግ የባለ ጉዳዩን ድርሻ ይሰጣል የሥራ ሂደቱን ቀሪ ሠነድ ያስተላልፋል