Government Service Requriements Government Service RequriementsGovernment Services Government Services

Back

የማይንቀሳቀሱ ንብረቶች /ቤት፣ሕንፃ፣የሊዝ መብት ሽያጭ/ ስጦታ ውል መስጠት

አገልግሎቱን ለማግኘት የሚያስፈልጉ መስፈርቶች

 • በህግ አግባብ የተዘጋጀ የውል ፅሁፍ /ፎርም/
 • የቤት ባለቤትነት ደብተር /ካርታ/ /ቤቱ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ክልል ውስጥ መሆን አለበት/
 • የዘመኑ የቦታና የቤት ግብር የተከፈለበት ደረሰኝ
 • የጋብቻ ማስረጃ ጋብቻ ከሌለ ይህንኑ የሚያረጋግጥ የቀበሌ አስተዳደር ወይም የማዘጋጃ ቤት ማስረጃ
 • በውርስ የተላለፈ ከሆነ የወራሽነት ማስረጃ
 • ውሉ የሊዝ መብት ማስተላለፍን የሚመለከት ከሆነ በተጨማሪ ከቤትና ከቦታ ግብር በስተቀር
 • ሻጩ በንግድ መዝገብ ላይ የተመዘገበ ከሆነ ከግብር ዕዳ ነፃ መሆኑን የሚያረጋግጥ አግባብ ካለው ግብር አስከፋይ መስሪያ ቤት ክሊራንስ ማቅረብ አለበት
 • ገዢው በትውልድ ኢትዮጵያዊና የውጭ አገር ዜጋ ከሆነ በትውልድ ኢትዮጵያዊ በመሆኑ የተሰጠው መታወቂያ
 • የሊዝ ውል
 • የሊዝ ቅድሚያ ክፍያ የተፈፀመበት ደረሰኝ

    አገልግሎቱን ለማግኘት የሚካሄዱ ሂደቶች

 1. ባለጉዳዩ ሠነዱ ተረጋግጦ እንዲመዘገብለት ጥያቄ ያቀርባል
 2. ስምሪትና መስተንግዶ ሠራተኛ አመጣጥኖ ያሠማራል
 3. የዕዳና ዕገዳ ማጣሪያ ሠራተኛ ከእዳ እገዳ ነፃ መሆኑን ያጣራል
 4. የሥራ ክፍሉ ሀላፊ ለህግና ለሞራል የማይቃረን መሆኑን ይመረምራል
 5. አጣሪና አፈራራሚ ሠራተኛ ያጣራል፣ ያፈራርማል ፣ይመዘግባል
 6. ገንዘብ ተቀባይ የአገልግሎትና የቴምብር ቀረጥ ክፍያ ያሰባስባል
 7. ሠነድ አረጋጋጭና መዝጋቢ ሠራተኛ ሰነዶችን በማያያዝና ማህተም በማድረግ ቁጥርና ቀን ይሰጣል 
 8. የስራ ክፍሉ ሀላፊ በመፈራረም ቲተሩን ያስቀምጣል
 9. የማህተምና ዕደላ ሠራተኛ በየገፁ ላይ ማህተም በማድረግ የባለ ጉዳዩን ድርሻ ይሠጣል የሥራ ሂደቱን ቀሪ ሠነድ ያስተላልፋል