Government Service Requriements Government Service RequriementsGovernment Services Government Services

Back

የብድር እዳ ስረዛ አገልግሎት ለሚፈልጉ

አገልግሉት ለማግኘት የሚያስፈልጉ መስፈርች

 • የብድር ዋስትና የሚመዘገበው የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ወይም ደብተር ያለው ሲሆን ብቻ ነው
 • ከአበዳሪው መስሪያ ቤት የብድር ውሉን መሸኛው በመ/ቤት አድራሻ ተጽፎ ሲቀርብ
 • ተወካይ ከሆነ የውክልና ውል እና የማንነት ማረጋገጫ መታወቂያ

አገልግሎቱን ለማግኘት የሚከናወኑ ሂደቶች

 1. ፎርም መውሰጃ ቢሮ በመሄድ የማጣሪያ ፎርም አገልግሎት በመውሰድ መሙላት
 2. የተሞላውን ፎርም በይዞታ አስተዳደር ቢሮ ማስገባት
 3. የተሞላውን ፎርም በዛው ቢሮ የሚገኝ ባለሙያ ይመረምራል
 4. ፎርሙን ከተመለከተ በኃላ ፋይል መጠየቂያ ካርድ ይሠጣቸዋል
 5. የፋይል ማውጫውን ካርድ በመያዝ  መዝገብ ቤት መስጠት
 6. መዝገብ ቤት መዝገቡን የይዞታ አስተዳደር ቢሮ በመውሰድ ለባለሙያው ይሠጣል
 7. ባለሙያው መዝገቡን በመመልከት የክፍያ ዝርዝር ያወጣል
 8. የወጣውን የክፍያ ዝርዝር ለባለጉዳዩ ይሠጠዋል 
 9. በዛው ቢሮ የአገልግሎት ክፍያ ይከናወናል
 10. የተከፈለውን ደረሰኝ በዛው ቢሮ ይገባል
 11. የሚመለከተው አካል የብድር እዳ ስረዛውን አገልግሎት ይሠጣል