Government Service Requriements Government Service RequriementsGovernment Services Government Services

Back

በህብረት ስራ ማህበራት ለመመዝገብ

አገልግሎቱን ለማግኘት መሟላት ያለባቸው መስፈርቶች

 • በጠቅላላው ጉባኤ አባላት የፀደቀ የመተዳደሪያ ደንብ
 • የአባላቱ ስም ዝርዝር እና አድራሻና ፊርማ
 • የህብረት ስራ ማህበሩ የስራ አመራር ኮሚቴ አባላት ስም ዝርዝር ሀላፊነት እድራሻና ፊርማ
 • የማህበሩ አመታዊ እቅድ 
 • የመነሻ ካፒታል መጠንና ገንዘቡ በባንክ ሂሳብ ቁጥር ገቢ መደረጉን የሚያስረዳ ማስረጃ 
 • ማህበሩ የሚመሠረትበት ቦታ መግለጫ
 • በማህበሩ ስም የተደራጁ የሂሳብ ሰነዶች የአባላት መዝገብ የንብረት መዝገብና ማህተም 
 • የአዋጪነት ጥናት ውጤት ሪፖርት
 • የማህበሩ መተዳደሪያ ደንብ

በዩኔን ለመደራጀት

 • ሁለትና ከዚያ በላይ የሆኑ መሠረታዊ ማህበራት ስምና ዝርዝር ሆኖ ከላይ የተዘረዘሩትን ጉዳዩች አሟልቶ መገኘት ይኖርበታል

በፌዴሬሽን ለመደራጀት

 • ሁለትና ከዚያ በላይ የሆኑ ዩኔየኖች ስምና ዝርዝር ሆኖ በተመሳሳይ በመሠረታዊ ማህበራት የተዘረዘሩትን መግለጫዎች ማቅረብ ይኖርበታል

አገልግሎቱን ለማግኘት የሚከናወኑ ሂደቶች

 1. ህብረት ስራ ማህበር በመሄድ ለመመዝገብ በጽሁፍ የተደገፈ የማደራጀት ጥያቄ ማቅረብ
 2. በዛው ቢሮ የሚገኝ ባለሙያ ማመልክቻውን ይመለከታል
 3. የህብረት ስራ ማህበር አደረጃጀት መመሪያዎች የተጠቀሱት የምዝገባ መሠረቶች መሟላታቸው ህጋዊነታይረጋገጣል
 4. በዛው ቢሮ የምዝገባ መዝገብ ላይ በመመዝገብ የመለያ ቁጥር ይሠጣቸዋል
 5. የሚመለከተው አካል ህጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ይሠጣቸዋል