Government Service Requriements Government Service RequriementsGovernment Services Government Services

Back

የንግድ ማህበራት መመስረቻ ፅሁፍ መተዳደሪያ ደንብ ማጽደቅ

አገልግሎቱን ለማግኘት መሟላት ያለባቸው መስፈርቶች

 • የቀበሌ ነዋሪነት መታወቂያ /ፓስፖርት/ ከፎቶ ኮፒ ጋር
 • የተዘጋጀ የመመስረቻ ጽሁፍና መተዳደሪያ ደንብ ረቂቅ
 • የማህበሩ ስም አለመያዙን ከንግድና ኢንዱስትሪ ሚ/ር ማረጋገጫ /ለጊዜው/
 • የአክሲዎን ማህበር ከሆነ የማህበሩ ¼ ካፒታል በዝግ ሂሳብ በማህበሩ ስም ስለመቀመጡ የባንክ ማረጋገጫ
 • አባላቱ ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በአካል በመቅረብ /ወኪል ከሆነ ህጋዊ ውክልና ማስረጃ ከፎቶ ኮፒው ጋር ማቅረብ/
 • ከአባላቶች መካከል የውጭ ዜጋ ካለ የኢንቨስትመንት ፈቃድና በህጋዊ መንገድ ሀገር ውስጥ ስለመግባቱ የሚያረጋግጥ /ፓስፖርት/ ከፎቶ ኮፒ ማቅረብ

አገልግሎቱን ለማግኘት የሚከናወኑ ሂደቶች

 1. የንግድ ምዝገባና ፈቃድ ኦፊሰር ቢሮ ማመልከቻ ማስገባት
 2. በዛው በሮ የሚገኝ ባለሙያ ማመልከቻውንና ከላይ የተገለፁትን መስፈርቶች ይመረምራል
 3. የሚመለከተው አካል መዝገብ እንዲከፈትላቸው ይደረጋል
 4. በዛው ቢሮ እንደ አገልግሎቱ የአገልገሎት ክፍያ እንዲከፈል ይደረጋል
 5. የተከፈለት ደረሰኝ በዛው ቢሮ ለሚገኝ ባለሙያ ይሠጣል
 6. የተከፈለት ደረሰኝ በመመልከት የንግድ ማህበር መመስርቻ ፁሁፍና መተዳደሪያ ደንብ ይፀድቃል