Government Service Requriements Government Service RequriementsGovernment Services Government Services

Back

የብድር፣የመያዣ ወይም የዋስትና ውል ጥያቄ ማስፈፀም

አገልግሎቱን ለማግኘት የሚያስፈልጉ መስፈርቶች

 • በህግ አግባብ የተዘጋጀ የውል ፅሁፍ /ፎርም/
 • በመያ¶ነት ወይም በዋስትና የተጠቀሰ ንብረት ካለ የባለቤትነት ማስረጃ
 • በህግ ግዴታ የተጣለበት የብድር የመያ¶ ወይም የዋስትና ውል ሲሆን የአበዳሪና የተበዳሪ የጋብቻ ማስረጃ ከሌለ አለመኖሩን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ከቀበሌ አስተዳደር ወይም ከማዘጋጃ ቤት

አገልግሎቱን ለማግኘት የሚካሄዱ ሂደቶች

 1. ሠነድ ተረጋግጦ እንዲመዘገብለት ጥያቄ ያቀርባል
 2. ስምሪትና መስተንግዶ ሠራተኛ አመጣጥኖ ያሠማራል
 3. ዕዳና ዕገዳ ማጣሪያ ሠራተኛ ከእዳና እገዳ ነፃ መሆኑን ያጣራል
 4. የስራ ክፍሉ ሀላፊ ለህግና ለሞራል የማይቃረን መሆኑን ይመረምራል
 5. አጣሪና አፈራራሚ አጣርቶ ካፈራረመ በኃላ ወደ ገንዘብ ቤት ይመራል
 6. ገንዘብ ተቀባይ የአገልግሎትና የቴምብር ቀረጥ ክፍያ ይሰበስባል
 7. ሠነድ አረጋጋጭና መዝጋቢ ሠራተኛ ሰነዶችን በማያያዝና ማህተም በማድረግ ቁጥርና ቀን በመስጠት ወደ ስራ ክፍሉ ሀላፊ ይመራል
 8. የስራ ክፍሉ ሀላፊ በመፈረም ቲተሩን ካስቀመጡ በኃላ ወደ የማህተምና የዕደላ ሠራተኛ ይመራል
 9. የማህተም የዕደላ ሠራተኛ በየገፁ ላይ ማህተም በማድረግ የባለ ጉዳዩን ድርሻ ይሰጣል የስራ ሂደቱን ቀሪ ሰነድ ያስተላልፋል